የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2 ዜና መዋዕል 3

3
ሰሎሞን ቤተ መቅደስ ሠራ
3፥1-14 ተጓ ምብ – 1ነገ 6፥1-29
1ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ላይ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ዳዊት ባዘጋጀው ቦታ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ። 2በነገሠም በአራተኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በሁለተኛው ቀን ቤተ መቅደሱን መሥራት ጀመረ።
3ሰሎሞን ለአምላክ ቤተ መቅደስ ሕንጻ የጣለው መሠረት በቀድሞው ስፍር ልክ ርዝመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱም ሃያ ክንድ#3፥3 ርዝመቱ 27 ሜትር ወርዱ 9 ሜትር ያህል ነው። ነበር። 4በቤተ መቅደሱ አዳራሽ ፊት ለፊት ያለው በረንዳ#3፥4 በዚህና በቍጥር 8 እንዲሁም 13 ላይ 9 ሜትር ያህል ነው። ርዝመቱ በቤተ መቅደሱ ወርድ ልክ ሃያ ክንድ ሲሆን፣ ከፍታውም ሃያ#3፥4 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞችና የሱርስቱ ቅጅ ከዚህ ጋራ ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን አንድ መቶ ሃያ ይላል። ክንድ ነበር።
ውስጡንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው። 5የቤተ መቅደሱን ዋና ክፍል በጥድ ዕንጨት አልብሶ በተጣራ ወርቅ ለበጠው፤ የዘንባባና የሰንሰለት አምሳልም ቀረጸበት። 6ቤተ መቅደሱን በከበረ ድንጋይ አስጌጠው፤ የተጠቀመበትም ወርቅ የፈርዋይም ወርቅ ነበር። 7የጣራውን ተሸካሚዎች፣ መቃኖችን፣ የቤተ መቅደሱን ግድግዳና መዝጊያዎች በወርቅ ለበጠ፤ በግድግዳዎቹም ላይ የኪሩቤልን ምስል ቀረጸ።
8እንደዚሁም ቅድስተ ቅዱሳኑን ሠራ፤ ርዝመቱ ከቤተ መቅደሱ ወርድ ጋራ እኩል ሲሆን፣ ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ስፋቱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ውስጡንም በስድስት መቶ#3፥8 21 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው። መክሊት የተጣራ ወርቅ ለበጠው። 9የወርቅ ምስማሮቹም ዐምሳ#3፥9 575 ግራም ያህል ነው። ሰቅል ይመዝኑ ነበር፤ የላይኛውንም ክፍሎች እንደዚሁ በወርቅ ለበጠ።
10በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የሁለት ኪሩቤል ምስል አስቀርጾ በወርቅ ለበጣቸው። 11ከዳር እስከ ዳር ገጥሞ የተዘረጋው የኪሩቤል ክንፍ በጠቅላላው ሃያ ክንድ ነበር፤ የመጀመሪያው ኪሩብ አንዱ ክንፍ ዐምስት ክንድ#3፥11 በዚህና በቍጥር 15 ላይ 2.3 ሜትር ያህል ነው። ሆኖ የቤተ መቅደሱን ግድግዳ ሲነካ፣ ሌላው ዐምስት ክንድ የሆነው ክንፉ ደግሞ የሁለተኛውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። 12እንደዚሁም የሁለተኛው ኪሩብ አንዱ ክንፍ ዐምስት ክንድ ሆኖ በአንጻሩ ያለውን የቤተ መቅደስ ግድግዳ ሲነካ፣ ዐምስት ክንድ የሆነው ሌላው ክንፉ ደግሞ የመጀመሪያውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። 13የተዘረጋው የእነዚህ ኪሩቤል ክንፍ ሃያ ክንድ ሲሆን፣ ፊታቸውን ወደ ቤተ መቅደሱ ዋና ክፍል አዙረው#3፥13 ወይም፣ ወደ ቤተ መቅደሱ እያዩ ተብሎ መተርጐም ይቻላል። በእግራቸው ቆመዋል።
14ደግሞም ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከደማቅ ቀይ ፈትልና ከቀጭን በፍታ መጋረጃ ሠርቶ፣ የኪሩቤልን ምስል በጥልፍ ጠለፈበት።
15በቤተ መቅደሱም ፊት ለፊት በአንድነት ቁመቱ ሠላሳ ዐምስት ክንድ#3፥15 16 ሜትር ያህል ነው። የሆነ፣ በእያንዳንዱም ላይ ዐምስት ክንድ ጕልላት ያለው ሁለት ዐምድ ሠራ። 16እርስ በርሳቸው የተጠላለፉ ሰንሰለቶች ሠርቶ#3፥16 ወይም፣ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሰንሰለት ሠርቶ ተብሎ መተርጐም ይችላል፤ በዕብራይስጡ የዚህ ሐረግ ትርጕም በትክክል አይታወቅም። ከዐምዶቹ ጫፍ ጋራ አገናኛቸው፤ ከዚያም መቶ የሮማን ፍሬዎች ሠርቶ ከሰንሰለቶቹ ጋራ አያያዛቸው። 17ዐምዶቹንም አንዱን በደቡብ፣ ሌላውን በሰሜን አድርጎ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በስተ ደቡብ ያቆመውን ዐምድ፣ “ያኪን”፣#3፥17 ምናልባት ያኪን ማለት፣ እርሱ አነጸ ማለት ሊሆን ይችላል። በስተሰሜን ያለውንም፣ “ቦዔዝ”#3፥17 ምናልባት ቦዔዝ ማለት ብርታት በርሱ ውስጥ ነው ማለት ሊሆን ይችላል። ብሎ ጠራቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ