የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ነገሥት 7

7
ሰሎሞን ቤተ መንግሥቱን ሠራ
1ሰሎሞን የራሱን ቤተ መንግሥት ሠርቶ ለመጨረስ ዐሥራ ሦስት ዓመት ፈጀበት። 2የሊባኖስ ዱር የተባለ ቤተ መንግሥት ሠራ፤ ይህም ርዝመቱ#7፥2 ርዝመቱ 46 ሜትር፣ ወርዱ 23 ሜትር እንዲሁም ቁመቱ 14 ሜትር ያህል ነው። መቶ ክንድ፣ ወርዱ ዐምሳ ክንድ፣ ቁመቱ ሠላሳ ክንድ ሲሆን፣ በአራት ረድፍ የቆሙ የዝግባ ምሰሶዎች ደግፈው የያዟቸው አግዳሚ የዝግባ ተሸካሚዎች ነበሩት። 3ቤቱ ከምሰሶዎቹ ላይ ያረፉ አግዳሚ ተሸካሚዎች አሉት፤ በእያንዳንዱ ዐምድ ላይ ዐሥራ ዐምስት፣ በድምሩ አርባ ዐምስት ተሸጋጋሪዎች ሲኖሩ፣ ከእነዚህም ተሸጋጋሪዎች በላይ ከዝግባ የተሠራ የጣሪያ ክዳን ነበር። 4መስኮቶቹም ከፍ ብለው የተሠሩ በሦስት ምድብ የተከፈሉና ትይዩ ነበሩ። 5በሮቹ በሙሉ ባለአራት ማእዘን መቃኖች ያሏቸው፣ በሦስት ምድብ የተከፈሉና ትይዩ#7፥5 በዕብራይስጥ የክፍሉ መልእክት በትክክል አይታወቅም። ነበሩ።
6ሰሎሞን፣ “ባለብዙ ምሰሶ አዳራሽ” የተባለ ቤት ሠራ፤ የዚህም ርዝመቱ ዐምሳ ክንድ፣ ወርዱ ሠላሳ ክንድ፣#7፥6 ርዝመቱ 23 ሜትር፣ ወርዱ 14 ሜትር ያህል ነው። ነበር፤ በስተ ፊት በኩልም ጣራ ያለውና በአዕማድ የተደገፈ መመላለሻ ነበረው።
7ዳኝነት የሚያይበትንም የዙፋን ችሎት አዳራሽ ሠራ፤ ይኸውም የፍትሕ አዳራሽ የተባለው ነው፤ ይህንም ከወለሉ አንሥቶ እስከ ጣራው#7፥7 ቩልጌትና የሱርስቱ ትርጕም ከዚህ ጋራ ሲስማሙ ዕብራይስጡ ግን፣ ወለል ይላል። ድረስ በዝግባ ሳንቃ ሸፈነው። 8ከአዳራሹ በስተጀርባ ባለው አደባባይ መኖሪያው እንዲሆን የተሠራው ቤተ መንግሥትም የዚሁ ተመሳሳይ ነበር። ሰሎሞን ላገባት ለፈርዖን ልጅ ይህንኑ ቤተ መንግሥት የመሰለ አዳራሽ ሠራ።
9ከውጭ አንሥቶ እስከ ትልቁ አደባባይ፣ ከመሠረቱ አንሥቶ እስከ ድምድማቱ ያለው የሕንጻ ሥራ በሙሉ፣ በውስጥም በውጭም በልክ በልኩ በተቈረጠና አምሮ በተጠረበ ምርጥ ድንጋይ የተሠራ ነበር። 10መሠረቱም ዐሥርና#7፥10 4.5 ሜትር ያህል ነው። በተጨማሪም በቍጥር 23 ላይ ይገኛል። ስምንት ክንድ#7፥10 3.6 ሜትር ያህል ነው። ርዝመት ባላቸውና ምርጥ በሆኑ ታላላቅ ድንጋዮች የተሠራ ነበር። 11በላዩም ላይ ምርጥ የሆኑ፣ በልክ በልኩ የተቈረጡ ድንጋዮችና የዝግባ ሳንቃዎች ነበሩ። 12እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጠኛ አደባባይ ከመመላለሻ በረንዳው ጭምር እንደ ትልቁ አደባባይ አምሮ በተጠረበ ሦስት ረድፍ ድንጋይና ተስተካክሎ በተከረከመ በአንድ ረድፍ የዝግባ ሳንቃ የታጠረ ነበር።
የቤተ መቅደሱ ዕቃዎች
7፥23-26 ተጓ ምብ – 2ዜና 4፥2-5
7፥387፥40-51 ተጓ ምብ – 2ዜና 4፥62፥10–5፥1
13ንጉሥ ሰሎሞንም መልእክተኛ ልኮ ኪራም#7፥13 ኪራም ዕብራይስጡ ሂራም ይለዋል። በተጨማሪም በቍጥር 40 እና 45 ላይ ይገኛል። የተባለውን ሰው ከጢሮስ አስመጣ፤ 14የኪራም እናት ከንፍታሌም ነገድ ስትሆን፣ እርሷም መበለት ነበረች፤ አባቱ የጢሮስ ሰው ሲሆን፣ የናስ ሥራ ባለሙያ ነበር። ኪራም በማናቸውም የናስ ሥራ ጥበብን፣ ማስተዋልንና ዕውቀትን የተሞላ ሰው ነበር፤ እርሱም ወደ ንጉሥ ሰሎሞን መጥቶ የተመደበለትን ሥራ ሁሉ አከናወነ።
15ኪራም የእያንዳንዱ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ፣ ዙሪያው ዐሥራ ሁለት ክንድ#7፥15 ቁመቱ 8.1 ሜትር፣ ዙሪያው 5.4 ሜትር ያህል ነው። የሆነ፣ ሁለት የናስ ምሰሶዎች ሠራ። 16እንዲሁም በምሰሶዎቹ ዐናት ላይ የሚሆኑ፣ ሁለት ጕልላት ከቀለጠ ናስ ሠራ፤ የእያንዳንዱም ጕልላት ቁመት ዐምስት ክንድ#7፥16 2.3 ሜትር ያህል ነው። በተጨማሪም በቍጥር 23 ላይ ይገኛል። ነበር። 17በምሰሶዎቹ ዐናት ላይ ላሉት ጕልላቶችም ጌጥ እንዲሆኑ፣ ለእያንዳንዳቸው ሰባት የመረብ ሰንሰለት አበጀ፤ 18ደግሞም በምሰሶዎቹ ላይ ያሉትን ጕልላቶች ለማስጌጥ የእያንዳንዱን መረብ ዙሪያ የሚከብቡ ሮማኖች በሁለት ረድፍ#7፥18 ሁለት የዕብራይስጥ ቅጆችና የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ከዚህ ጋራ ሲስማሙ፣ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ በሁለት ረድፍ አዕማዶች ሥራ ይላሉ። ሠራ፤ ለሁለቱም ጕልላቶች#7፥18 ብዙ የዕብራይስጥ ቅጆችና የሱርስቱ ትርጕም ከዚህ ጋራ ሲስማሙ፣ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን ሮማኖች ይላሉ። ያደረገው ተመሳሳይ ነበር። 19በመመላለሻው ምሰሶዎች ዐናት ላይ ያሉት ጕልላቶች ቁመታቸው አራት ክንድ#7፥19 1.8 ሜትር ይላል። በተጨማሪም በቍጥር 38 ላይ ይገኛል። ሲሆን፣ የሱፍ አበባ ቅርጽ ነበራቸው። 20በሁለቱም የምሰሶ ጕልላቶችና ከመርበቡ ቀጥሎ ባለው የክብ ቅርጽ ላይ ዙሪያውን በሙሉ ሁለት መቶ ሮማኖች በተርታ ነበሩ። 21ዐምዶቹንም በቤተ መቅደሱ መመላለሻ ላይ አቆመ፤ በስተ ደቡብ ያቆመውን ዐምድ “ያኪን”፣#7፥21 ምናልባት አነጸ ማለት ሊሆን ይችላል። በስተሰሜን በኩል ያለውንም “ቦዔዝ”#7፥21 ምናልባት በርሱ ዘንድ ጥንካሬ አለ ማለት ሊሆን ይችላል ብሎ ጠራው። 22ዐናቱ ላይ ያሉት ጕልላቶች የሱፍ አበባ ቅርጽ ነበራቸው። የምሰሶዎቹም ሥራ በዚህ ሁኔታ ተፈጸመ።
23ቅርጹ ክብ፣ ስፋቱ ከጠርዝ እስከ ጠርዝ ዐሥር ክንድ፣#7፥23 4.5 ሜትር ያህል ነው። ቁመቱ ዐምስት ክንድ የሆነ ክብ ገንዳ ከቀለጠ ብረት ሠራ፤ ዙሪያውም ሲለካ ሠላሳ ክንድ#7፥23 14 ሜትር ያህል ነው። ሆነ። 24ከገንዳው ከንፈር በታችም፣ በእያንዳንዱ ክንድ ላይ እንደ ቅል ያሉ ዐሥር ቅርጾች ዙሪያውን በሁለት ረድፍ ከብበውታል፤ እነዚህም ከገንዳው ጋራ አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ተሠርተው ነበር።
25ገንዳውም፣ ሦስቱ ፊታቸውን ወደ ሰሜን፣ ሦስቱ ወደ ደቡብ፣ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፣ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ባዞሩ የዐሥራ ሁለት በሬዎች ምስሎች ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ ገንዳው በላያቸው ሆኖ የሁሉም የኋላ አካል በመካከል ላይ የገጠመ ነበር። 26የገንዳው ውፍረት አንድ ስንዝር#7፥26 7.5 ሴንቲ ሜትር ያህል ነው። ሲሆን፣ የከንፈሩ ጠርዝ ደግሞ የአበባ ቅርጽ ያለው የጽዋ ከንፈር የመሰለ ነው፤ ይህም ሁለት ሺሕ የባዶስ መስፈሪያ#7፥26 44 000 ሊትር ያህል ነው። የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ይህን ዐረፍተ ነገር አይጨምርም። ያህል ውሃ የሚይዝ ነበር።
27እንዲሁም ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ዐሥር ባለመንኰራኵር የዕቃ ማስቀመጫዎች ከመዳብ ሠራ፤ የእያንዳንዱም ርዝመት አራት ክንድ፣ ወርድ አራት ክንድ፣ ቁመትም ሦስት ክንድ#7፥27 ርዝመቱና ወርዱ 1.8 ሜትር ያህል ሲሆን ቁመቱ 1.4 ሜትር ያህል ነው። ነበር። 28የዕቃ ማስቀመጫዎቹ የተሠሩት እንደዚህ ነው፤ እነዚህም ቀጥ ብለው ከቆሙ ደጋፊዎች ጋራ የተያያዙ ባለአራት ማእዘን ጠፍጣፋ ናሶች ነበሯቸው። 29ዳርና ዳር ባሉት ድጋፎች መካከል በሚገኙት ጠፍጣፋ ናሶች ላይ የአንበሶችን፣ የኰርማዎችንና የኪሩቤልን ምስል አደረገ፤ በድጋፎቹም ላይ እንደዚሁ አደረገ። ከአንበሶቹና ከኰርማዎቹ በላይና በታች በኩል ደግሞ የአበባ ጕንጕን የሚመስሉ ተቀጥቅጠው የተሠሩ ቅርጾች ነበሩ። 30እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ አራት የናስ መንኰራኵርና መንኰራኵሮቹ የሚሽከረከሩባቸው የናስ ወስከምቶች እንዲሁም እያንዳንዳቸው በአራቱም ማእዘን ገጽ ላይ የአበባ ጕንጕን ቀልጦ የተሠራባቸው የመታጠቢያ ገንዳ መደገፊያዎች ነበረው። 31በዕቃ ማስቀመጫዎቹም ውስጥ ጥልቀቱ አንድ ክንድ#7፥31 45 ሳንቲ ሜትር ያህል ነው። የሆነ ባለክብ ክፍተት ነበር፤ ይህም ክፍተት ድቡልቡል ሆኖ ከታች ከመቆሚያው በኩል ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል#7፥31 68 ሳንቲ ሜትር ያህል ነው። በተጨማሪም በቍጥር 32 ላይ ይገኛል። ወርድ ሲኖረው፣ በክፍተቱም ዙሪያ ቅርጾች ነበሩ፤ ክፈፎቹ ግን ባለአራት ማእዘን እንጂ ክብ አልነበሩም። 32አራቱ መንኰራኵሮች በዕቃ ማስቀመጫው ጠፍጣፋ ናስ ሥር ሲሆኑ፣ የመንኰራኵሮቹ ወስከምቶች ደግሞ ከዕቃ ማስቀመጫዎቹ ጋራ የተያያዙ ነበሩ፤ የእያንዳንዱም መንኰራኵር ስፋት አንድ ክንድ ተኩል ነበር። 33መንኰራኵሮቹ የሠረገላ መንኰራኵር መሰል ሲሆኑ፣ ወስከምቶቹ የመንኰራኵሮቹ ክፈፎችና ዐቃፊዎቻቸው እንዲሁም ወስከምቶቹ የሚገቡባቸው ቧንቧዎች በሙሉ ከቀለጠ ብረት የተሠሩ ነበሩ።
34እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ አራት ወጣ ያለ እጀታ ነበረው። 35በዕቃ ማስቀመጫው ጫፍ ላይ ግማሽ ክንድ#7፥35 23 ሳንቲ ሜትር ያህል ነው። የሆነ ዙሪያ ክብ ነበረበት፤ ድጋፎቹና ጠፍጣፋ ናሶቹ ከዕቃ ማስቀመጫው ዐናት ጋራ የተያያዙ ነበሩ። 36እርሱም በድጋፎቹና በጠፍጣፋ ናሶቹ ላይ ባለው ቦታ ሁሉ፣ ዙሪያውን የአበባ ጕንጕን እያደረገ ኪሩቤልን፣ አንበሶችንና የዘንባባ ዛፎችን ቀረጸ። 37ዐሥሩም የዕቃ ተሸካሚዎች የተሠሩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ሁሉም ከአንድ ቅርጽ ቀልጠው የወጡ ስለ ሆነ፣ በመጠንና በቅርጽ ፍጹም ተመሳሳይ ነበሩ።
38ከዚያም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ የሚሆን፣ እያንዳንዱ አርባ የባዶስ መስፈሪያ የሚይዝ ዐሥር የናስ መታጠቢያ ገንዳ ሠራ፤ ስፋቱም አራት ክንድ ነበር። 39ከዕቃ ማስቀመጫዎቹም ዐምስቱን ከመቅደሱ በስተ ደቡብ፣ ዐምስቱን በስተሰሜን በኩል አኖረ፤ ገንዳውንም ከቤተ መቅደሱ በደቡብ ምሥራቅ ጫፍ ላይ በስተ ደቡብ አኖረው። 40ኪራምም ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ሠራ።
ኪራምም ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራውን ሥራ ሁሉ ፈጸመ እነዚህም፦
41ሁለቱን አዕማድ፣
በአዕማዱ ጫፎች ላይ ያሉትን ሁለት ባለሳሕን ጕልላቶችን፤
በአዕማዱ ላይ ያሉትን ባለሳሕን ቅርጽ ሁለት ጕልላቶችን ያስጌጡትን ሁለት መረቦች፤
42በአዕማዱ ጫፎች ላይ ያሉትን ባለሳሕን ቅርጽ ጕልላቶች የሚሸፍኑና በሁለት ረድፍ የተቀረጹትን መረቦች የሚያስጌጡትን አራት መቶ ሮማኖች፤
43ዐሥሩን የዕቃ ማስቀመጫዎች፣ ከዐሥር መታጠቢያ ገንዳዎቻቸው ጋራ፤
44ገንዳውና ከሥሩ ያሉትን ዐሥራ ሁለት ኰርማዎች፤
45ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን እና ጐድጓዳ ሳሕኖችን።
ኪራም ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ እንዲሆኑ እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራለት ከሚብረቀረቅ ናስ ነበር። 46ንጉሡም እነዚህ ዕቃዎች በዮርዳኖስ ሸለቆ፣ በሱኮትና በጻርታን መካከል ባለው በሸክላ ዐፈር ቦታ ቀልጠው በሸክላ ቅርጽ ተሠርተው እንዲወጡ አደረገ። 47ሰሎሞን ከብዛታቸው የተነሣ እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች እንዲመዘኑ አላደረገም፣ ስለዚህም የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደ ነበር አልታወቀም።
48እንደዚሁም ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ የሚሆኑትን ዕቃዎች ሠራ፤ እነዚህም፦
የወርቅ መሠዊያ፣
የገጸ ኅብስቱ ጠረጴዛ፣
49በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ዐምስቱ በቀኝ፣ ዐምስቱ በግራ የሚቀመጡ፣ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መቅረዞችን፣ ከወርቅ የተቀረጹ አበቦችን፣ ቀንዲሎችንና መኰስተሪያዎችን፤
50ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ጽዋዎችን#7፥50 ወይም ሳሕኖች፣ የመብራት መኰስተሪያዎችን፣ ለመርጫ የሚሆኑ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፣ ጭልፋዎችን፣
የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎችን፣ ለውስጠኛው ክፍል ለቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችና እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ በሮች የሚሆኑ የወርቅ ማጠፊያዎችን።
51ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሠራው ሥራ ሁሉ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ አባቱ ዳዊት የቀደሰውን ብሩንና ወርቁን፣ ዕቃዎቹንም ሁሉ አምጥቶ በእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት አኖራቸው።

Currently Selected:

1 ነገሥት 7: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ