የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ቆሮንቶስ 14:3-5

1 ቆሮንቶስ 14:3-5 NASV

ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽ፣ ለማበረታታትና ለማጽናናት ለሰው ይናገራል። በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ቤተ ክርስቲያንን ያንጻል። ሁላችሁም በልሳን ብትናገሩ እወድዳለሁ፤ ከዚህ ይልቅ ግን ትንቢትን ብትናገሩ እወድዳለሁ። ቤተ ክርስቲያን እንድትታነጽ በልሳን የሚናገር ሰው የተናገረውን ካልተረጐመ፣ በልሳን ከሚናገር ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል።