የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ዜና መዋዕል 3

3
የዳዊት ወንዶች ልጆች
3፥1-4 ተጓ ምብ – 2ሳሙ 3፥2-5
3፥5-8 ተጓ ምብ – 2ሳሙ 5፥14-161ዜና 14፥4-7
1ዳዊት በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤
የበኵር ልጁ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም፣
ሁለተኛው ዳንኤል፣ ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ፣
2ሦስተኛው ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣
አራተኛው የአጊት ልጅ አዶንያስ፣
3ዐምስተኛው የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያ፣
ስድስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም።
4እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት ዳዊት በኬብሮን ሆኖ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ጊዜ ነበር።
ዳዊት በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፤ 5በኢየሩሳሌም የተወለዱለትም ልጆች እነዚህ ነበሩ፤
ሳሙስ፣#3፥5 ዕብራይስጡ፣ ሺማ ይላል፤ ሻሙአ ከሚለው ጋራ አንድ ነው። ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፤ እነዚህ አራት ወንዶች ልጆች ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ#3፥5 አንድ የዕብራይስጡ ጽሑፍና ቩልጌት (በተጨማሪም ሰብዓ ሊቃናት እና 2ሳሙ 11፥3 ይመ)፤ ብዙ የዕብራይስጥ ጽሑፎች ቤርሹሃ ይላሉ። የተወለዱ ናቸው።
6ኢያቤሐር፣ ኤሊሳማ#3፥6 ሁለት የዕብራይስጥ ጽሑፎች (2ሳሙ 5፥15 እና 1ዜና 14፥5 ይመ)፤ ብዙ የዕብራይስጥ ጽሑፎች ኤሊሻማ ይላሉ።፣ ኤሊፋላት፣ 7ኖጋ፣ ናፌቅ፣ ያፍያ፣ 8ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባላሉ፤ በአጠቃላይ ዘጠኝ ነበሩ።
9ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ የዳዊት ልጆች ነበሩ፤ እነዚህም ትዕማር የምትባል እኅት ነበረቻቸው።
የይሁዳ ነገሥታት
10የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ነበረ፤
የሮብዓም ልጅ አብያ፣
የአብያ ልጅ አሳ፣
የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣
11የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም፣
የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣
የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ፣
12የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ፣
የአሜስያስ ልጅ ዓዛርያስ፣
የዓዛርያስ ልጅ ኢዮአታም፣
13የኢዮአታም ልጅ አካዝ፣
የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ፣
የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ፣
14የምናሴ ልጅ አሞን፣
የአሞን ልጅ ኢዮስያስ።
15የኢዮስያስ ወንዶች ልጆች፤
በኵሩ ዮሐናን፣
ሁለተኛ ልጁ ኢዮአቄም፣
ሦስተኛ ልጁ ሴዴቅያስ፣
አራተኛ ልጁ ሰሎም።
16የኢዮአቄም ዘሮች፤
ልጁ ኢኮንያ፣
ልጁ ሴዴቅያስ።
ከምርኮ በኋላ የነበረው የነገሥታቱ የትውልድ ሐረግ
17የምርኮኛው የኢኮንያን ዘሮች፤
ልጁ ሰላትያል፣ 18መልኪራም፣ ፈዳያ፣ ሼናጻር፣ ይቃምያ፣ ሆሻማ፣ ነዳብያ።
19የፈዳያ ወንዶች ልጆች፤
ዘሩባቤል፣ ሰሜኢ።
የዘሩባቤል ወንዶች ልጆች፤
ሜሱላም፣ ሐናንያ፤ እኅታቸው ሰሎሚት ትባላለች። 20ሌሎችም ዐምስት ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም ሐሹባ፣ ኦሄል፣ በራክያ፣ ሐሳድያ፣ ዮሻብሒሴድ።
21የሐናንያ ዘሮች፤
ፈላጥያ፣ የሻያ፤ እንዲሁም የረፋያ፣ የአርናን፣ የአብድዩና የሴኬንያ ወንዶች ልጆች።
22የሴኬንያ ዘሮች፤
ሸማያና ወንዶች ልጆቹ፤ ሐጡስ፣ ይግአል፣ ባሪያሕ፣ ነዓርያ፣ ሻፋጥ፤ በአጠቃላይ ስድስት ነበሩ።
23የነዓርያ ወንዶች ልጆች፤
ኤልዮዔናይ፣ ሕዝቅያስ፣ ዓዝሪቃም፤ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ።
24የኤልዮዔናይም ወንዶች ልጆች፤
ሆዳይዋ፣ ኤልያሴብ፣ ፌልያ፣ ዓቁብ፣ ዮሐናን፣ ደላያ፣ ዓናኒ፤ በአጠቃላይ ሰባት ናቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ