የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ዜና መዋዕል 1

1
ከአዳም እስከ አብርሃም ያለው የትውልድ ሐረግ እስከ ኖኀ ልጆች
1አዳም፣ ሴት፣ ሄኖስ፣
2ቃይናን፣ መላልኤል፣ ያሬድ፣
3ሔኖክ፣ ማቱሳላ፣ ላሜሕ፣ ኖኅ።
4የኖኅ ወንዶች ልጆች#1፥4 የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ ዕብራይስጡ ግን፣ የኖኀ ወንዶች ልጆች የሚለውን አይጨምርም።፤ ሴም፣ ካም፣ ያፌት።
ያፌታውያን
1፥5-7 ተጓ ምብ – ዘፍ 10፥2-5
5የያፌት ልጆች#1፥5 ልጆች ማለት ዘርዐ ትውልዶች ወይም ወራሾች ወይም ሕዝቦች ማለት ሊሆን ይችላል፤ ከ6-9፣ 17 እና በ23 ይገኛል።፦ ጎሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሜሼኽ፣ ቴራስ።
6የጎሜር ልጆች፤
አስከናዝ፣ ሪፋት#1፥6 በተጨማሪም ዘፍ 10፥3 ይመ። በብዙ የዕብራይስጥ ጽሑፎች ዲፋት ይላሉ።፣ ቶጋርማ።
7የያዋን ልጆች፤
ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮድኢ።
ካማውያን
1፥8-16 ተጓ ምብ – ዘፍ 10፥6-20
8የካም ወንዶች ልጆች፤
ኵሽ፣ ምጽራይም፣#1፥8 ግብጽ ናት፤ እንዲሁም ቍ11 ፉጥ፣ ከነዓን።
9የኵሽ ወንዶች ልጆች፤
ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰብቃታ።
የራዕማ ወንዶች ልጆች፤
ሳባ፣ ድዳን።
10ኵሽ ናምሩድን አባት#1፥10 አባት ማለት ቅድመ አያት ወይም እንጅላት ወይም መሠረት ማለት ነው፤ እንዲሁም ቍ 16። ነበረ፤
እርሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኀያል ጦረኛ ሆነ።
11ምጽራይም፦ የሉዳማውያን፣ የዐናሚማውያን፣ የላህቢያውያን፣ የነፍተሂማውያን፣ 12የፈትሩሲማውያን፣ ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው፣ የከስሉሂማውያንና የቀፍቶሪማውያን አባት ነበረ።
13ከነዓንም፦ የበኵር ልጁ
የሲዶን፣ የኬጢያውያን፣ 14የኢያቡሳውያን፣ የአሞራውያን፣ የጌርጌሳውያን፣ 15የኤዊያውያን፣ የዐርካውያን፣ የሲኒውያን፣ 16የአራዴዎያውያን፣ የሰማሪናውያንና የአማቲያውያን አባት ነበረ።
ሴማውያን
1፥17-23 ተጓ ምብ – ዘፍ 10፥21-3111፥10-27
17የሴም ልጆች፤
ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው።
የአራም ልጆች፤#1፥17 በአንድ የዕብራይስጥ ቅጅ እና በአንድ አንድ የሰባ ሊቃናት ቅጆች ብቻ ላይ የሚገኝ ሐረግ ነው።
ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሜሼኽ።
18አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤
ሳላም ዔቦርን ወለደ።
19ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤
አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፋሌቅ#1፥19 ፋሌቅ ማለት ክፍፍል ማለት ነው። ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።
20ዮቅጣንም፦
አልሞዳድን፣ ሣሌፍን፣ ሐስረሞትን፣ ያራሕን፣ 21ሀዶራምን፣ አውዛልን፣ ደቅላን፣ 22ዖባልን፣#1፥22 አንዳንድ የዕብራይስጥ ቅጆችና የሱርስቱ ትርጕም (እንዲሁም ዘፍ 10፥28 ይመ) ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ ብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ዒባል ይላሉ። አቢማኤልን፣ ሳባን፣ 23ኦፊርን፣ ኤውላጥን፣ ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ናቸው።
24ሴም፣ አርፋክስድ#1፥24 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ቅጆች ግን፣ አርፋክስድ፣ ቃይንም ይላሉ (የዘፍ 11፥10 ይመ)።፣ ሳላ፣
25ዔቦር፣ ፋሌቅ፣ ራግው፣
26ሴሮሕ፣ ናኮር፣ ታራ፣
27እንዲሁም በኋላ አብርሃም የተባለው አብራም።
የአብርሃም ቤተ ሰብ
28የአብርሃም ወንዶች ልጆች፤ ይሥሐቅ፣ እስማኤል።
የአጋር ዘሮች
1፥29-31 ተጓ ምብ – ዘፍ 25፥12-16
29ዘሮቻቸው እነዚህ ናቸው፤
የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብዳኤል፣ መብሳም፣ 30ማስማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣ ኩዳን፣ ቴማን፣ 31ኢጡር፣ ናፌስና ቄድማ፤
እነዚህ የእስማኤል ወንዶች ልጆች ናቸው።
የኬጡራ ዘሮች
1፥32-33 ተጓ ምብ – ዘፍ 25፥1-4
32የአብርሃም ቁባት ኬጡራ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ዘምራን፣ ዮቅሳን፣ ሜዳን፣ ምድያም፣ የስቦቅና፣ ስዌሕ ናቸው።
የዮቅሳን ወንዶች ልጆች፤
ሳባ፣ ድዳን።
33የምድያም ልጆች፦
ጌፌር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው።
እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው።
የሣራ ዘሮች
1፥35-37 ተጓ ምብ – ዘፍ 36፥10-14
34አብርሃም ይሥሐቅን ወለደ።
የይሥሐቅ ወንዶች ልጆች፤
ዔሳው፣ እስራኤል።
የዔሳው ወንዶች ልጆች
35የዔሳው ወንዶች ልጆች፤
ኤልፋዝ፣ ራጉኤል፣ የዑስ፣ የዕላም፣ ቆሬ።
36የኤልፋዝ ወንዶች ልጆች፤
ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ#1፥36 ብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች፣ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞችና የሱርስቱ ቅጅ (እንዲሁም ዘፍ 36፥11 ይመ) ከዚህ ጋራ ይስማማሉ፤ አያሌ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ጾፊ ይላሉ።፣ ጎቶም፣
ቄኔዝ፣ ቲምናዕ፣ አማሌቅ።
37የራጉኤል ወንዶች ልጆች፤
ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማና ሚዛህ።
በኤዶም የሚኖሩ የሴይር ሰዎች
1፥38-42 ተጓ ምብ – ዘፍ 36፥20-28
38የሴይር ወንዶች ልጆች፤
ሎጣን፣ ሦባል፣ ፂብዖን፣ ዓና፣ ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን።
39የሎጣን ወንዶች ልጆች፦
ሖሪና ሄማም፤ ቲምናዕ የሎጣን እኅት ነበረች።
40የሦባል ወንዶች ልጆች፦
ዓልዋን#1፥40 ብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች፣ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞችና የሱርስቱ ቅጅ (እንዲሁም ዘፍ 36፥23 ይመ) ከዚህ ጋራ ይስማማሉ፤ አያሌ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ኣሊያን ይላሉ።፣ ማኔሐት፣ ዔባል፣ ስፎ እና አውናም።
የፂብዖን ወንዶች ልጆች፤
አያ እና ዓና።
41የዓና ወንድ ልጅ፤
ዲሶን።
የዲሶን ወንዶች ልጆች፤
ሐምዳን#1፥41 ብዙ የዕብራይስጥና አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች (እንዲሁም ዘፍ 36፥26) ከዚህ ጋራ ይስማማሉ፤ አያሌ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ሐምራን ይላሉ።፣ ኤስባን፣ ይትራን እና ክራን።
42የኤጽር ወንዶች ልጆች፤
ቢልሐን፣ ዛዕዋን እና ዓቃን#1፥42 ዘፍ 36፥28 ይመ።
የዲሶን ወንዶች ልጆች፤
ዑፅ እና አራን።
የኤዶምያስ ነገሥታት
1፥43-54 ተጓ ምብ – ዘፍ 36፥31-43
43በእስራኤል ምንም ንጉሥ ከመንገሡ በፊት#1፥43 ወይም፣ እስራኤላዊ የሆነ ንጉሥ ገና በእነርሱ ላይ ከመንገሡ በፊት በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤
የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።
44ባላቅ ሲሞት፣ የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በምትኩ ነገሠ።
45ኢዮባብ ሲሞት፣ የቴማን አገር ሰው ሑሳም በምትኩ ነገሠ።
46ሑሳም ሲሞት፣ በሞዓብ ምድር ምድያማውያንን ድል ያደረገው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ። የከተማውም ስም ዓዊት ተባለ።
47ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ።
48ሠምላ ሲሞት በወንዙ#1፥48 ምናልባት ኤፍራጥስን ነው። አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኡል በምትኩ ነገሠ።
49ሳኡል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን በምትኩ ነገሠ።
50በኣልሐናን ሲሞት ሃዳድ በምትኩ ነገሠ። የእርሱም ከተማ ስም ፋዑ#1፥50 ብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች፣ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞችና የሱርስቱ ቅጅ እና ቩልጌት (እንዲሁም ዘፍ 36፥39 ይመ) ከዚህ ጋራ ይስማማሉ፤ አያሌ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ፓይ ይላሉ። ነው፤ የሚስቱም ስም መሄጣብኤል ሲሆን እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የማጥሬድ ልጅ ነበረች። 51ሃዳድም ሞተ።
ዋና ዋናዎቹ የኤዶም ሕዝብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤
ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣ 52ኦሆሊባማ፣ ኤላ፣ ፒኖን፣ 53ቄናዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣ 54መግዲኤል እና ዒራም።
እነዚህ የኤዶም ዘሮች የነገድ አለቆች ነበሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ