1
ትንቢተ ኢሳይያስ 25:1
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አቤቱ፥ አንተ አምላኬ ነህ፥ ድንቅን ነገር የዱሮ ምክርን በታማኝነትና በእውነት አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ስምህንም አመሰግናሁ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 25:8
ሞትን ለዘላለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፥ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 25:9
በዚያም ቀን፦ እነሆ፥ አምላካችን ይህ ነው፥ ተስፋ አድርገነዋል፥ ያድነንማል፥ እግዚአብሔር ይህ ነው፥ ጠብቀነዋል፥ በማዳኑ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን ይባላል።
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 25:7
በዚህም ተራራ ላይ በወገኖች ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፥ በአህዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል።
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 25:6
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ የጥሩና ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።
Home
Bible
Plans
Videos