1
ወደ ሮሜ ሰዎች 4:20-21
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እግዚአብሔር ያናገረለትንም ተስፋ ይቀራል ብሎ አልተጠራጠረም፤ በእምነት ጸና እንጂ፤ ለእግዚአብሔርም ክብርን ሰጠ። እግዚአብሔርም የሰጠውን ተስፋ ሊያደርግለት እንደሚችል በፍጹም ልቡ አመነ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 4:17
“ለብዙዎች አሕዛብ አባት አደርግሃለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ ሙታንን በሚያስነሣቸው፥ የሌሉትንም እንደ አሉ በሚያደርጋቸው በአመነበት በእግዚአብሔር ፊት አብርሃም የሁላችን አባት ነው።
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 4:24-25
ስለ ኀጢአታችን የተሰቀለውን፥ ሊያስነሣንና ሊያጸድቀን የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ለይቶ በአስነሣው ስለምናምን ስለ እናም ነው እንጂ።
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 4:18
አብርሃም “ዘርህ እንዲሁ ይሆናል” ብሎ እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠው ተስፋ ባልነበረ ጊዜ የብዙዎች አሕዛብ አባት እንደሚሆን አመነ።
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 4:16
ስለዚህም እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሩ የሰጠው ተስፋ የታመነ ይሆን ዘንድ፥ የሚጸድቁ በእምነት እንጂ የኦሪትን ሥራ በመፈጸም ብቻ እንዳይደለ ያውቁ ዘንድ እግዚአብሔር ጽድቅን በእምነት አደረገ።
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 4:7-8
“መተላለፋቸው የቀረላቸው፥ ኀጢአታቸውም የተሰረየላቸው ብፁዓን ናቸው። እግዚአብሔርም በደሉን የማይቈጥርበት ሰው ብፁዕ ነው።”
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 4:3
መጽሐፍስ ምን ይላል? አብርሃም በእግዚአብሔር አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።
Home
Bible
Plans
Videos