1
መጽሐፈ ምሳሌ 12:25
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
የሚያስደነግጥ ቃል የጻድቅ ሰው ልቡናን ያውካል፤ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 12:1
ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤ ተግሣጽን የሚጠላ ግን ሰነፍ ነው።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 12:18
በሐሰት የሚመሰክሩ በሰይፍ ይገድላሉ፤ በአፋቸው ሰይፍ አለና። የጠቢባን ምላስ ግን የቈሰለውን ይፈውሳል።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 12:15
የሰነፎች መንገድ በፊታቸው የቀናች ናት፤ ጠቢብ ግን ምክርን ይሰማል።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 12:16
ሰነፍ ቍጣውን በየቀኑ ይናገራል፤ ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 12:4
ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ ክፉ ሴት ግን ነቀዝ እንጨትን እንደሚበላ እንዲዚሁ ባሏን ትጐዳለች።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 12:22
ሐሰተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።
8
መጽሐፈ ምሳሌ 12:26
ራሱን የሚያውቅ ሰው ለራሱ ጻድቅ ነው፤ የክፉዎች ሥራ ግን መልካም አይደለም። የሚበድሉ ሰዎችን ክፉ ይከተላቸዋል፥ የኃጥኣን መንገዳቸውም ታስታቸዋለች።
9
መጽሐፈ ምሳሌ 12:19
የጻድቃን ከንፈሮች ምስክርነትን ያቀናሉ፥ የሚቸኩል ምስክር ግን ክፉ አንደበት አለው።
Home
Bible
Plans
Videos