1
ኦሪት ዘኍልቍ 21:8
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “የናስ እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል፤ እባቡም ሰውን ቢነድፍ የተነደፈው ሁሉ ይመልከተው፤ ይድናልም” አለው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ኦሪት ዘኍልቍ 21:9
ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ፤ እባብም የነደፈችው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ።
3
ኦሪት ዘኍልቍ 21:5
ሕዝቡም፥ “በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣኸን?” ብለው እግዚአብሔርንና ሙሴንም አሙ። “እንጀራ የለም፤ ውኃም የለምና፥ ሰውነታችንም ይህን ጥቅም የሌለው እንጀራ ተጸየፈች” ብለው ተናገሩ።
4
ኦሪት ዘኍልቍ 21:6
እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ የሚገድሉ እባቦችን ሰደደ፤ ሕዝቡንም ነደፉ፤ ከእስራኤልም ልጆች ብዙ ሰዎች ሞቱ።
5
ኦሪት ዘኍልቍ 21:7
ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው፥ “በእግዚአብሔርና በአንተ ስለ ተናገርን በድለናል፤ እባቦችን ከእኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን” አሉት። ሙሴም ስለ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
Home
Bible
Plans
Videos