1
ኦሪት ዘኍልቍ 13:30
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ካሌብም ሕዝቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰኘና፥ “አይደለም! ማሸነፍን እንችላለንና እንውጣ፤ እንውረሳት” አለ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ኦሪት ዘኍልቍ 13:33
በዚያም ግዙፋን የሆኑትን አየን፤ እኛም በእነርሱ ፊት እንደ አንበጣዎች ሆን፤ እንዲሁም በፊታቸው ነበርን፤” እያሉ የሰለሉአትን ምድር ለእስራኤል ልጆች አስፈሪ አደረጓት።
3
ኦሪት ዘኍልቍ 13:31
ከእርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን ፥ “በኀይል ከእኛ ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም” አሉ።
4
ኦሪት ዘኍልቍ 13:32
ስለ ሰለሉአትም ምድር ለእስራኤል ልጆች እያወሩ፥ “እኛ ዞረን የሰለልናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ምድር ናት፤ በእርስዋም ዘንድ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ረጃጅም ሰዎች ናቸው፤
5
ኦሪት ዘኍልቍ 13:27
እንዲህም ብለው ነገሩት፥ “ወደ ላክኸን ምድር ደረስን፤ እርስዋም ወተትና ማር ታፈስሳለች፤ ፍሬዋም ይህ ነው።
6
ኦሪት ዘኍልቍ 13:28
ነገር ግን በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ኀያላን ናቸው፤ ከተሞቻቸውም የተመሸጉ፥ እጅግም የጸኑ ታላላቅ ናቸው።
7
ኦሪት ዘኍልቍ 13:29
ደግሞም በዚያ የዔናቅን ዘሮች አየን፤ በአዜብ በኩል ዐማሌቅ ተቀምጦአል፤ በተራሮችዋም ኬጤዎናዊውና ኤዌዎናዊውም፥ ኢያቡሴዎናዊው፥ አሞሬዎናዊውም ተቀምጠዋል፤ ከነዓናዊውም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ተቀምጦአል።”
8
ኦሪት ዘኍልቍ 13:26
ገሥግሠውም በቃዴስ ፋራን ምድረ በዳ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ደረሱ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።
Home
Bible
Plans
Videos