1
የያዕቆብ መልእክት 3:17
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
የያዕቆብ መልእክት 3:13
ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ሥራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ።
3
የያዕቆብ መልእክት 3:18
የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል።
4
የያዕቆብ መልእክት 3:16
ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ አሉና።
5
የያዕቆብ መልእክት 3:9-10
በእርሱ ጌታንና አብን እናመሰግናለን፤ በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን፤ ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ! ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።
6
የያዕቆብ መልእክት 3:6
አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በሰውነታችን ክፍሎች መካከል ዐመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፤ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፤ በገሃነምም ይቃጠላል።
7
የያዕቆብ መልእክት 3:8
ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው።
8
የያዕቆብ መልእክት 3:1
ወንድሞቼ ሆይ! ከእናንተ ብዙዎቹ አስተማሪዎች አይሁኑ፤ የባሰውን ፍርድ እንድንቀበል ታውቃላችሁና።
Home
Bible
Plans
Videos