1
ትንቢተ ኢሳይያስ 42:6-7
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
“እኔ እግዚአብሔር አምላክ በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፤ በእጄም እይዝሃለሁ፤ አበረታሃለሁም፤ ለልጅ ልጅ ቃል ኪዳን፥ ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ። የዕውራንንም ዐይን ትከፍት ዘንድ፥ የተጋዙትንም ከግዞት ቤት፥ በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 42:8
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 42:1
እነሆ፥ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ ያዕቆብ፤ ነፍሴ የተቀበለችው ምርጤ እስራኤልም፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያመጣል።
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 42:3-4
የተቀጠቀጠ ሸንበቆን አይሰብርም፤ የሚጤስንም ክር አያጠፋም፤ ነገር ግን በእውነት ፍርድን ያመጣል። በምድርም ፍርድን እስኪያደርግ ድረስ ያበራል እንጂ አይጠፋም፤ አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 42:16
ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ የማያውቋትንም ጎዳና እንዲረግጡ አደርጋቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህንም አደርግላቸዋለሁ፤ አልተዋቸውምም።
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 42:9
እነሆ የቀድሞው ነገር ተፈጸመ፤ አዲስ ነገርንም እናገራለሁ፤ አስቀድሞም ሳይነገር እርሱን አስታውቃችኋለሁ።”
Home
Bible
Plans
Videos