1
መጽሐፈ መክብብ 9:10
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መክብብ 9:11
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሓይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ጦርነትም ለኀያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለዐዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገናኛቸዋል።
3
መጽሐፈ መክብብ 9:9
በሕይወትህ፥ አንተም ከፀሓይ በታች በምትደክምበት ድካም ይህ ዕድል ፈንታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀሓይ በታች በሰጠህ፥ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ፥ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።
4
መጽሐፈ መክብብ 9:7
እግዚአብሔር ሥራህን ተቀብሎታልና፦ ና እንጀራህን በደስታ ብላ፥ በበጎ ልቡናም የወይን ጠጅህን ጠጣ።
5
መጽሐፈ መክብብ 9:18
ከጦር መሣሪያዎች ይልቅ ጥበብ ትሻላለች፤ አንድ ኀጢአተኛ ግን ብዙ መልካምን ያጠፋል።
6
መጽሐፈ መክብብ 9:17
በስንፍና ከሚፈርዱ ፈራጆች ጩኸት ይልቅ የጠቢባን ቃል በጸጥታ ትሰማለች።
7
መጽሐፈ መክብብ 9:5
ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን አንዳች አያውቁም፤ መታሰቢያቸውም ተረስቶአልና ከዚህ በኋላ ዋጋ የላቸውም።
Home
Bible
Plans
Videos