1
ኦሪት ዘዳግም 5:16
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህ አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ኦሪት ዘዳግም 5:33
በሕይወት እንድትኖሩ፥ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።”
3
ኦሪት ዘዳግም 5:9-10
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ።
4
ኦሪት ዘዳግም 5:8
“በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር ማንኛውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤
5
ኦሪት ዘዳግም 5:7
“ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
6
ኦሪት ዘዳግም 5:11
“የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በሐሰት አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በሐሰት የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።
7
ኦሪት ዘዳግም 5:29
ለእነርሱ፥ ለዘለዓለምም ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ፥ እንዲፈሩኝ፥ ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ እንዲጠብቁ እንዲህ ያለ ልብ ማን በሰጣቸው፥
8
ኦሪት ዘዳግም 5:12
“ዕለተ ሰንበትን ጠብቅ፤ እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህም ቀድሳት።
9
ኦሪት ዘዳግም 5:21
“የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ፤ የባልንጀራህንም ቤት፥ እርሻውንም፥ ሎሌውንም፥ ገረዱንም፥ በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።
10
ኦሪት ዘዳግም 5:18
“ነፍስ አትግደል።
11
ኦሪት ዘዳግም 5:20
“በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር፤ ምስክርንም አታሳብል።
12
ኦሪት ዘዳግም 5:17
“አታመንዝር።
13
ኦሪት ዘዳግም 5:19
“አትስረቅ።
14
ኦሪት ዘዳግም 5:15
አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ አስብ፤ እግዚአብሔር አምላክህ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ አወጣህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ዕለተ ሰንበትን ትጠብቃትና ትቀድሳት ዘንድ አዘዘህ።
15
ኦሪት ዘዳግም 5:13-14
ስድስት ቀን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፥ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ እንደምታርፍ ሎሌህና ገረድህ ያርፉ ዘንድ፥ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ በሬህም፥ አህያህም፥ ከብትህም ሁሉ፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ መጻተኛ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ።
16
ኦሪት ዘዳግም 5:6
“ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ።
Home
Bible
Plans
Videos