1
ኦሪት ዘዳግም 28:1
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
“እንዲህም ይሆናል፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽመህ ብትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ፥ ብትጠብቅም፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ኦሪት ዘዳግም 28:2
የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡልሃል፤ ያገኙህማል።
3
ኦሪት ዘዳግም 28:13
ዛሬም ያዘዝሁህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሰምተህ ብትጠብቃት፥ ብታደርጋትም፥ እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁልጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም።
4
ኦሪት ዘዳግም 28:12
እግዚአብሔርም ለምድርህ በወራቱ ዝናብን ይሰጥ ዘንድ፥ የእጅህንም ሥራ ሁሉ ይባርክ ዘንድ መልካሙን መዝገብ ሰማዩን ይከፍትልሃል፤ ለብዙ አሕዛብም ታበድራለህ፥ አንተ ግን ከማንም አትበደርም፤ ብዙ አሕዛብን ትገዛለህ፥ አንተን ግን እነርሱ አይገዙህም።
5
ኦሪት ዘዳግም 28:7
“እግዚአብሔርም ከእግርህ በታች ይወድቁ ዘንድ የሚቃወሙህን ጠላቶችህን በእጅህ ይጥላቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፤ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ።
6
ኦሪት ዘዳግም 28:8
እግዚአብሔር በረከቱን በአንተ ላይ፥ በጎተራህ፥ በእህልህም ሥራ ሁሉ እንዲወርድ ይልካል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ይባርክሃል።
7
ኦሪት ዘዳግም 28:6
አንተም በመግባትህ ቡሩክ ትሆናለህ፥ በመውጣትህም ቡሩክ ትሆናለህ።
8
ኦሪት ዘዳግም 28:3
አንተ በከተማ ቡሩክ ትሆናለህ፤ በእርሻም ቡሩክ ትሆናለህ።
9
ኦሪት ዘዳግም 28:4
የሆድህ ፍሬ፥ የምድርህም ፍሬ፥ የከብትህም ፍሬ፥ የላምህም መንጋ፥ የበግህም መንጋ ቡሩክ ይሆናል።
10
ኦሪት ዘዳግም 28:9
የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትሰማ፥ በመንገዱም ብትሄድ፥ እግዚአብሔር ለአባቶችህ እንደ ማለ ለእርሱ የተቀደሰ ሕዝብ አድርጎ ያቆምሃል።
11
ኦሪት ዘዳግም 28:5
መዛግብትህና የቀረውም ሁሉ ቡሩክ ይሆናል።
12
ኦሪት ዘዳግም 28:11
አምላክህ እግዚአብሔርም እርስዋን ይሰጥህ ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው በምድርህ ላይ፥ በሆድህ ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ ከብቶችህን በማብዛት እግዚአብሔር በጎነቱን ያበዛልሃል።
13
ኦሪት ዘዳግም 28:10
የምድር አሕዛብም ሁሉ የአምላክህ የእግዚአብሔር ስም በአንተ ላይ እንደ ተጠራ አይተው ይፈሩሃል።
14
ኦሪት ዘዳግም 28:14
ዛሬም ካዘዝሁህ ከእነዚህ ቃሎች ወደ ቀኝ፥ ወደ ግራም ፈቀቅ ባትል፥ ታመልካቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት ባትከተል።
15
ኦሪት ዘዳግም 28:15
“ነገር ግን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ሁሉ ባትጠብቅ፥ ባታደርግም፥ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይመጡብሃል፤ ያገኙህማል።
Home
Bible
Plans
Videos