1
ኦሪት ዘዳግም 1:30-31
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
በፊታችሁ የሚሄደው አምላካችሁ እግዚአብሔር፥ በግብፅ ምድር እንዳደረገላችሁ ሁሉ፥ ስለ እናንተ አብሮአችሁ ይዋጋል፤ ወደዚህም ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ፥ ሰው ልጁን እንዲመግብ አምላካችሁ እግዚአብሔር በምድረ በዳ እንደመገባችሁ እናንተ አይታችኋል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ኦሪት ዘዳግም 1:11
የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በዚህ ቍጥር ላይ እልፍ አእላፋት ይጨምር፤ እንደ ተናገራችሁም ይባርካችሁ።
3
ኦሪት ዘዳግም 1:6
“አምላካችን እግዚአብሔር በኮሬብ እንዲህ ብሎ ተናገረን፦ በዚህ ተራራ መቀመጣችሁ በቃ፤
4
ኦሪት ዘዳግም 1:8
እነሆ፥ ምድሪቱን ሰጠኋችሁ፤ ግቡ፥ እግዚአብሔር ለእነርሱ፥ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውን ምድር ውረሱ።
5
ኦሪት ዘዳግም 1:17
በፍርድም ፊት አትዩ፤ ለትልቁም፥ ለትንሹም በእውነት ፍረዱ፤ ለሰው ፊት አታድሉ፤ ፍርድ የእግዚአብሔር ነውና። አንድ ነገር ቢከብዳችሁ እርሱን ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም እሰማዋለሁ፤
Home
Bible
Plans
Videos