1
የዮሐንስ ራእይ 20:15
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ሁሉ በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
የዮሐንስ ራእይ 20:12
ሙታንን፥ እንዲሁም ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላም መጽሐፍ ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት በተጻፈው መሠረት፥ እንደ ሥራቸው መጠን ፍርድን ተቀበሉ።
3
የዮሐንስ ራእይ 20:13-14
ባሕርም በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን አስረከበ፤ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ዘንድ ያሉትን ሙታን አስረከቡ፤ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ፍርድን ተቀበለ። ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።
4
የዮሐንስ ራእይ 20:11
ታላቅና ነጭ ዙፋን፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።
5
የዮሐንስ ራእይ 20:7-8
ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፤ በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን ለማሳትና ለጦርነት ለማስከተት ይወጣል፤ ቁጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ ነው።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች