1
መዝሙረ ዳዊት 139:14
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፥ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መዝሙረ ዳዊት 139:23-24
አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም እወቅ፥ ፈትነኝ መንገዴንም እወቅ፥ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ፥ የዘለዓለምንም መንገድ ምራኝ።
3
መዝሙረ ዳዊት 139:13
አቤቱ፥ አንተ ኩላሊቴን ፈጥረሃልና፥ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል።
4
መዝሙረ ዳዊት 139:16
ያልተሠራ አካሌን ዐይኖችህ አዩ፥ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ።
5
መዝሙረ ዳዊት 139:1
አቤቱ፥ መረመርኸኝ፥ አወቅኸኝም።
6
መዝሙረ ዳዊት 139:7
ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?
7
መዝሙረ ዳዊት 139:2
አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቅህ፥ ሐሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ።
8
መዝሙረ ዳዊት 139:4
የዓመፃ ቃል በአንደበቴ እንደሌለ።
9
መዝሙረ ዳዊት 139:3
ጉዞዬንና መኝታዬን አንተ መረመርህ፥ መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ፥
Home
Bible
Plans
Videos