1
መጽሐፈ ምሳሌ 3:5-6
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
በፍጹም ልብህ በጌታ ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፥ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 3:7
በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፥ ጌታን ፍራ፥ ከክፋትም ራቅ፥
3
መጽሐፈ ምሳሌ 3:9-10
ከሀብትህ አስበልጠህ ጌታን አክብር፥ ከፍሬህም ሁሉ በኵራት ይልቅ፥ ጐተራህም እህልን ይሞላል፥ መጥመቂያህም በወይን ጠጅ ሞልታ ትትረፈረፋለች።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 3:3
ደግነትና እውነት አይተዉህ፥ በአንገትህ ላይ እሰራቸው፥ በልብህ ጽላት ጻፋቸው።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 3:11-12
ልጄ ሆይ፥ የጌታን ተግሣጽ አትናቅ፥ በገሠጸህም ጊዜ አትመረር። ጌታ የወደደውን ይገሥጻልና፥ አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 3:1-2
ልጄ ሆይ፥ ሕጌን አትርሳ፥ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ። ብዙ ቀኖች፥ የሕይወት ዓመታትና ሰላምም ይጨምሩልሃልና።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 3:13-15
ጥበብን የሚያገኝ ሰው ብጹዕ ነው፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ ሰው፥ በእርሷ የሚገኘው ትርፍ ከብር ከሚገኘው፥ ገቢዋም ከወርቅ ይሻላልና። ከውድ ዕንቁም ትከብራለች፥ ከምትመኘው ነገር አንዳችም አይተካከላትም።
8
መጽሐፈ ምሳሌ 3:27
ልታደርግለት የሚቻልህ ሲሆን፥ ለተቸገረው ሰው በጎ ነገርን ከማድረግ አትቆጠብ።
9
መጽሐፈ ምሳሌ 3:19
ጌታ በጥበብ ምድርን መሠረተ፥ በማስተዋልም ሰማያትን አጸና።
Home
Bible
Plans
Videos