1
መጽሐፈ ኢዮብ 1:20-22
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ኢዮብም ተነሣ መጐናጸፊያውንም ቀደደ፥ ራሱንም ተላጨ፥ በምድርም ላይ ተደፍቶ ሰገደ፥ እንዲህም አለ፦ “ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፥ ጌታ ሰጠ፥ ጌታ ወሰደ፥ የጌታ ስም የተባረከ ይሁን።” በዚህ ሁሉ ኢዮብ አልበደለም፥ እግዚአብሔርንም አላማረረም።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ኢዮብ 1:1
ዖፅ በሚባል አገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ነበረ።
3
መጽሐፈ ኢዮብ 1:8
ጌታም ሰይጣንን፦ “በውኑ አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም” አለው።
4
መጽሐፈ ኢዮብ 1:12
ጌታም ሰይጣንን፦ “እነሆ ለእርሱ ያለው ሁሉ በእጅህ ነው፥ ነገር ግን በእርሱ ላይ እጅህን አትዘርጋ” አለው። ሰይጣንም ከጌታ ፊት ወጣ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች