1
መጽሐፈ መክብብ 1:18
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
በጥበብ መብዛት ትካዜ ይበዛልና፥ እውቀትንም የሚጨምር ኀዘንን ይጨምራልና።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መክብብ 1:9
የሆነው ነገር ወደፊትም የሚሆነው ነው፥ የተደረገውም ነገር ወደ ፊት የሚደረገው ነው፥ ከፀሐይም በታች ምንም አዲስ ነገር የለም።
3
መጽሐፈ መክብብ 1:8
ነገር ሁሉ ያደክማል፥ ሰው ይናገረው ዘንድ አይችልም፥ ዐይን ከማየት አይጠግብም፥ ጆሮም ከመስማት አይሞላም።
4
መጽሐፈ መክብብ 1:2-3
ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፥ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል። ከፀሐይ በታች በሚደክምበት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምንድነው?
5
መጽሐፈ መክብብ 1:14
ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም መከተል ነው።
6
መጽሐፈ መክብብ 1:4
ትውልድ ይሄዳል፥ ትውልድም ይመጣል፥ ምድር ግን ለዘለዓለም ናት።
7
መጽሐፈ መክብብ 1:11
ለፊተኞቹም ነገሮች መታሰቢያ የላቸውም፥ ለኋለኞቹም ነገሮች ከእነርሱ በኋላ በሚነሡት ሰዎች ዘንድ መታሰቢያ አይገኝላቸውም።
8
መጽሐፈ መክብብ 1:17
ጥበብንና ዕብደትን ሞኝነትንም አውቅ ዘንድ ልቤን ሰጠሁ፥ ይህም ደግሞ ነፋስን መከተል እንደሆነ አስተዋልሁ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች