1
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:37
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
አምላኬ ሆይ! ይህ ሕዝብ አንተ እውነተኛ አምላክ መሆንህንና ወደ አንተም ያቀረብከው አንተ ራስህ መሆንህን እንዲያውቅ እባክህ መልስ ስጠኝ፤ አምላክ ሆይ፥ ስማኝ!”
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:36
ከቀትር በኋላ የሠርክ መሥዋዕት በሚቀርብበት ሰዓት ነቢዩ ኤልያስ ወደ መሠዊያው ቀርቦ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ጌታ ሆይ! አንተ የእስራኤል አምላክ መሆንክን፥ እኔም የአንተ አገልጋይ መሆኔን፥ እኔም ይህን ሁሉ ያደረግኹት በቃልህ መሠረት መሆኑን አንተ ራስህ ግለጥ፤
3
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:21
ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ ጌታ እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!” አላቸው፤ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም።
4
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:38
ከዚህ በኋላ ጌታ እሳትን ላከ፤ ያም እሳት መሥዋዕቱን፥ እንጨቱንና ድንጋዩን አቃጠለ፤ ምድሩንም ለበለበ፤ በጉድጓዱ የነበረውንም ውሃ አደረቀ፤
5
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:39
ሰዎቹም ይህን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው በመደነቅ “ጌታ አምላክ ነው! እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ ነው!” አሉ።
6
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:44
በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ “ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ” አለው። ኤልያስም “ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ‘ዝናቡ ሳያቋርጥህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ’ ብለህ ንገረው” ሲል አዘዘው።
7
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:46
የጌታም ኃይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን በወገቡ ዙሪያ ጠበቅ አድርጎ በመታጠቅ እስከ ኢይዝራኤል መግቢያ በር ድረስ በአክዓብ ፊት ቀድሞ ይሮጥ ነበር።
8
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:41
ከዚህ በኋላ ኤልያስ ንጉሥ አክዓብን “እንግዲህ ሄደህ እህልና ውሃ ቅመስ፤ እኔ አሁን የከባድ ዝናም ነጐድጓድ ድምፅ መቃረቡን እየሰማሁ ነው” አለው።
9
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:43
አገልጋዩን፥ “ሂድና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት!” አለው። አገልጋዩም ሄዶ ሲመለስ “ምንም ነገር አይታየኝም” አለው፤ አገልጋዩ እየተመላለሰ ያይ ዘንድ ኤልያስ ሰባት ጊዜ አዘዘው።
10
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:30
ከዚህ በኋላ ኤልያስ ሰዎቹን “ወደ እኔ ቅረቡ” አላቸው፤ ሁሉም በዙሪያው ተሰበሰቡ፤ እርሱም ፈርሶ የነበረውን የጌታ መሠዊያ በማደስ ሠራው።
11
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:24
ከዚህ በኋላ የባዓል ነቢያት ወደ አምላካቸው ይጸልዩ፤ እኔም ወደ ጌታ እጸልያለሁ፤ እሳትን ወደ መሥዋዕቱ በመላክ መልስ የሚሰጥ እርሱ እውነተኛ አምላክ ነው።” ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድርጎ በዚህ ሐሳብ መስማማቱን ገለጠ።
12
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:31
ጌታ ከዚያ በፊት “እስራኤል” ብሎ ከሰየመው ከያዕቆብ በተወለዱት በዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ስም ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ወሰደ።
13
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:27
እኩለ ቀን ሲሆን ኤልያስ “ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጸልዩ! እርሱ አምላክ አይደለም እንዴ እርሱ በሐሳብ ተውጦ ይሆናል! ወይም ራሱን ያዝናና ይሆናል! ወይም ወደ ሩቅ አገር ሄዶ ይሆናል! ወይም ተኝቶ ያንቀላፋ ይሆናልና እንዲነቃ ቀስቅሱት!” እያለ ያፌዝባቸው ጀመር።
14
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:32
እነዚህንም ድንጋዮች ረብርቦ በጌታ ስም መሠዊያ ሠራ፤ በዙሪያውም ዐሥራ አራት ሊትር ውሃ የሚይዝ ጉድጓድ ማሰ።
Home
Bible
Plans
Videos