1
ወደ ቲቶ 1:16
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
“እግዚአብሔርን እናውቃለን” ይላሉ፤ በሥራቸው ግን ይክዱታል፤ እነርሱ አጸያፊዎች፥ የማይታዘዙና ምንም መልካም ሥራ ማድረግ የማይችሉ ናቸው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ወደ ቲቶ 1:15
ለንጹሖች፥ ሁሉ ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኩሶችና ለማያምኑ ሰዎች ግን ንጹሕ የሆነ ምንም ነገር የለም፤ እንዲያውም አእምሮአቸውም ሆነ ኅሊናቸው የረከሰ ነው።
3
ወደ ቲቶ 1:9
እውነተኛውን ትምህርት በማስተማር ለመምከርና ለተቃዋሚዎችም መልስ ለመስጠት እንዲችል በተማረው መሠረት በአስተማማኝ ቃል ይጽና።
4
ወደ ቲቶ 1:7-8
ኤጲስ ቆጶስ (የቤተ ክርስቲያን መሪ) የእግዚአብሔርን ሥራ በዐደራ የተቀበለ ስለ ሆነ የማይነቀፍ መሆን አለበት፤ እንዲሁም የማይኰራ፥ በቶሎ የማይቈጣ፥ የማይሰክር፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ለገንዘብ የማይስገበገብ መሆን አለበት። ይልቅስ እንግዳ ተቀባይ፥ መልካም የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ራሱን የሚቈጣጠር፥ ትክክለኛ፥ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ፥ በመጠን የሚኖር ይሁን።
5
ወደ ቲቶ 1:6
የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ የማይነቀፍና የአንዲት ሚስት ባል የሆነ፥ ስድ በመሆንና ባለመታዘዝ ምክንያት የማይወቀሱ አማኞች ልጆች ያሉት ሰው መሆን ይገባዋል።
Home
Bible
Plans
Videos