1
መጽሐፈ መዝሙር 34:18
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ልባቸው ለተሰበረ እግዚአብሔር ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መዝሙር 34:4
የእግዚአብሔርን ርዳታ ፈለግኹ እርሱም ሰማኝ፤ ከምፈራውም ነገር ሁሉ አዳነኝ።
3
መጽሐፈ መዝሙር 34:19
ጻድቅ ብዙ መከራ ይደርስበታል፤ እግዚአብሔር ግን ከዚህ ሁሉ ያድነዋል።
4
መጽሐፈ መዝሙር 34:8
የእግዚአብሔርን ደግነት እዩና ቅመሱ፤ እርሱን ከለላ ያደረገ የተባረከ ነው።
5
መጽሐፈ መዝሙር 34:5
ወደ እርሱ የሚመለከቱ ሁሉ ፊታቸው ይበራል፤ ፊታቸውም ከቶ በኀፍረት አይሸፈነም።
6
መጽሐፈ መዝሙር 34:17
ጻድቃን ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፤ እርሱም ይሰማቸዋል፤ ከችግራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል።
7
መጽሐፈ መዝሙር 34:7
የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች ይጠብቃል፤ በዙሪያቸውም ሆኖ ከአደጋ ያድናቸዋል።
8
መጽሐፈ መዝሙር 34:14
ከክፉ ነገር ሽሹ፤ መልካም ነገርንም አድርጉ፤ ሰላምን ፈልጉአት፤ ተከተሉአትም።
9
መጽሐፈ መዝሙር 34:13
እንግዲያውስ መጥፎ ነገር ከማውራትና ሐሰት ከመናገር ተቈጠቡ።
10
መጽሐፈ መዝሙር 34:15
እግዚአብሔር ወደ ጻድቃን ይመለከታል፤ ጸሎታቸውንም ያደምጣል።
11
መጽሐፈ መዝሙር 34:3
የእግዚአብሔርን ታላቅነት ከእኔ ጋር አስታውቁ፤ በኅብረትም ስሙን እናክብር።
Home
Bible
Plans
Videos