1
መጽሐፈ መዝሙር 103:2
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! ቸርነቱንም አትርሺ!
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መዝሙር 103:3-5
ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር ይላል፤ ሕመሜንም ሁሉ ይፈውሳል። ወደ መቃብር ከመውረድ ይጠብቀኛል፤ በፍቅርና በምሕረትም ይባርከኛል። በጐልማሳነቴ ሕይወቴን በመልካም ነገር ሁሉ ይሞላታል፤ እንደ ንስርም ወጣትነቴን ያድሳል።
3
መጽሐፈ መዝሙር 103:1
ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! የእግዚአብሔርን ቅዱስ ስም በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ።
4
መጽሐፈ መዝሙር 103:13
አባት ለልጆቹ የሚራራላቸውን ያኽል እግዚአብሔርም የሚፈሩትን ይራራላቸዋል።
5
መጽሐፈ መዝሙር 103:12
ምሥራቅ ከምዕራብ የሚርቀውን ያኽል እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ከእኛ ያርቀዋል።
6
መጽሐፈ መዝሙር 103:8
እግዚአብሔር መሐሪና ይቅር ባይ ነው። በቶሎ የማይቈጣና ለዘለዓለም ታማኝ ነው።
7
መጽሐፈ መዝሙር 103:10-11
በኃጢአታችን መጠን አልቀጣንም፤ በበደላችንም ልክ አልከፈለንም። ሰማይ ከምድር ከፍ የሚለውን ያኽል እግዚአብሔር ለሚፈሩት የሚሰጠው ፍቅር ታላቅ ነው።
8
መጽሐፈ መዝሙር 103:19
የእግዚአብሔር ዙፋን በሰማይ ነው፤ የእርሱም ገዢነት በሁሉም ላይ ነው።
Home
Bible
Plans
Videos