1
መጽሐፈ ምሳሌ 6:16-19
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤ እንዲያውም እርሱ የሚጸየፋቸው ሰባት ሲሆኑ እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፦ በንቀት የሚመለከት ዐይን፥ ሐሰትን የሚናገር ምላስ፥ ንጹሖች ሰዎችን የሚገድሉ እጆች፥ ክፉ ሐሳብ የሚያፈልቅ አእምሮ፥ ወደ ክፋት ለመሮጥ የሚቸኲሉ እግሮች፥ በውሸት ላይ ውሸት እየጨመረ የሚናገር ምስክር፥ በወዳጆች መካከል ጠብ የሚያነሣሣ ሰው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 6:6
አንተ ሰነፍ ወደ ጒንዳን ሄደህ መንገድዋን ተመልክተህ ጥበብን ቅሰም።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 6:10-11
“ጥቂት እተኛለሁ፤ ጥቂት አንቀላፋለሁ፤ እጄንም አጣጥፌ ለጥቂት ጊዜ ዐርፋለሁ” ስትል፥ ገና ተኝተህ ሳለ ድኽነትና ማጣት የጦር መሣሪያ እንደ ታጠቀ ወንበዴ በድንገት ይደርሱብሃል።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 6:20-21
ልጄ ሆይ! የአባትህን ትእዛዞች ፈጽም፤ እናትህ ያስተማረችህንም ከቶ አትተው፤ የእነርሱን መመሪያ ዘወትር ተከተል፤ ቃላቸውንም ዘወትር ጠብቅ፤
Home
Bible
Plans
Videos