1
መጽሐፈ ምሳሌ 23:24
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
የጨዋ ልጅ አባት ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፤ ብልኅ ልጅ የወለደም ሰው ኲራት ይሰማዋል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 23:4
ለመበልጸግ አትድከም፤ ከዚህ ዐይነት ስግብግብነት ለመራቅ ጥበበኛ ሁን፤
3
መጽሐፈ ምሳሌ 23:18
ይህን ብታደርግ የወደፊት ኑሮህ የተቃና ይሆናል፤ ተስፋህም አያቋርጥም።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 23:17
በኃጢአተኞች ላይ አትቅና፤ እግዚአብሔርን መፍራት የዘወትር ሐሳብህ ይሁን፤
5
መጽሐፈ ምሳሌ 23:13
ልጅን በሥነ ሥርዓት ከመቅጣት አትቦዝን፤ በአርጩሜ ብትመታው አይሞትም፤
6
መጽሐፈ ምሳሌ 23:12
አእምሮህን በትምህርት ላይ፥ ጆሮህንም ዕውቀትን በመስማት ላይ አውላቸው።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 23:5
እንዲህ ዐይነቱ ሀብት እያየኸው ወዲያው ይጠፋል፤ በሰማይ እንደ ሚበርር ንስር ክንፍ አውጥቶ ይበራል።
8
መጽሐፈ ምሳሌ 23:22
የወለደህ እርሱ ስለ ሆነ የአባትህን ምክር ስማ፤ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።
Home
Bible
Plans
Videos