1
መጽሐፈ ምሳሌ 22:6
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ልጅን እንዴት መኖር እንደሚገባው ብታስተምረው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 22:4
እግዚአብሔርን መፍራትና ትሑት መሆን ሀብት፥ ክብርና ሕይወትን ያስገኛል።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 22:1
መልካም ስም ከብዙ ሃብት ይሻላል፤ በሰው ዘንድ መወደድም ከብር ወይም ከወርቅ ይበልጣል።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 22:24
ከንዴተኛና ከቊጡ ሰው ጋር ባልንጀራ አትሁን፤
5
መጽሐፈ ምሳሌ 22:9
ምግቡን ከድኾች ጋር ስለሚካፈል ለጋሥ ሰው የተባረከ ይሆናል።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 22:3
ብልኅ ሰው አደጋ ሲመጣ አይቶ ይሸሸጋል። ማስተዋል የጐደለው ሰው ግን ሰተት ብሎ ወደ መከራ በመግባት ይጐዳል።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 22:7
ድኻ የሀብታም ሰው አገልጋይ ነው፤ ገንዘብ የሚበደር የአበዳሪው ባሪያ ነው።
8
መጽሐፈ ምሳሌ 22:2
ሀብታምንም ሆነ ድኻን የፈጠራቸው እግዚአብሔር ስለ ሆነ ሁለቱም በዚህ አንድ ናቸው።
9
መጽሐፈ ምሳሌ 22:22-23
ምንም ስለሌላቸው፥ ድኾችን አትበዝብዝ፤ የተጨቈኑትንም ሰዎች በፍርድ ሸንጎ አታጒላላ፤ ይኸውም እግዚአብሔር ስለሚከራከርላቸውና የሚያስጨንቁአቸውንም ስለሚያስጨንቅ ነው።
Home
Bible
Plans
Videos