1
መጽሐፈ ምሳሌ 21:21
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ጽድቅንና ቸርነትን የሚከተል ሰው ሕይወትን፥ ብልጽግናንና ክብርን ያገኛል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 21:5
በጥንቃቄ በወጣ ዕቅድ የሚሠራ ሥራ ትርፍ ያስገኛል፤ ያለ ዕቅድ በችኰላ የሚሠራ ሥራ ግን ያደኸያል።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 21:23
ከመከራ ለማምለጥ የሚፈልግ፥ ክፉ ከመናገር ይቈጠባል።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 21:2
ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን የልብን ሐሳብ ይመዝናል።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 21:31
ፈረስን ለጦርነት ማዘጋጀት ይቻላል፤ ድልን የሚያጐናጽፍ ግን እግዚአብሔር ነው።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 21:3
መሥዋዕት ከማቅረብ እውነተኛ ይልቅ ትክክልና የሆነውን ነገር ማድረግ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 21:30
ሰው በጥበቡ፥ በአስተዋይነቱና በዕቅዱ በእግዚአብሔር ላይ መነሣት አይችልም።
8
መጽሐፈ ምሳሌ 21:13
የድኾችን ጩኸት ለመስማት ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው እርሱም ተቸግሮ በሚጮኽበት ጊዜ የሚረዳው አያገኝም።
Home
Bible
Plans
Videos