1
መጽሐፈ ምሳሌ 19:21
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ሰዎች ብዙ ነገር ያቅዳሉ፤ ተፈጻሚነትን የሚያገኘው ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 19:17
ለድኾች የሚሰጥ ለእግዚአብሔር እንዳበደረ ይቈጠራል፤ እግዚአብሔርም የመልካም ሥራውን ዋጋ ይከፍለዋል።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 19:11
የቊጣን ስሜት መቈጣጠር አስተዋይነት ነው፤ ለበደለም ይቅርታ ማድረግ ጨዋነት ነው።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 19:20
ምክርን ብትሰማና ለመማርም ፈቃደኛ ብትሆን የኋላ ኋላ ጥበብ መገብየትህ አይቀርም።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 19:23
እግዚአብሔርን ብትፈራ ረጅም ዕድሜ ይኖርሃል፤ ጒዳት ሳይደርስብህ በደስታና በሰላም ትኖራለህ።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 19:8
ጥበብን የሚገበይ ሰው ራሱን ይወዳል፤ ዕውቀትን አጥብቆ የሚይዝ ይበለጽጋል።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 19:18
የመመለስ ተስፋ ሳላቸው ልጆችህን በልጅነታቸው ቅጣቸው፤ ባትቀጣቸው ግን ለጥፋት አሳልፈህ እንደ ሰጠሃቸው ይቈጠራል።
8
መጽሐፈ ምሳሌ 19:9
በሐሰት የሚመሰክር ሰው ሳይቀጣ አይቀርም፤ ሐሰትንም የሚናገር ጥፋት ያገኘዋል።
Home
Bible
Plans
Videos