1
መጽሐፈ ምሳሌ 17:17
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ወዳጅ ምን ጊዜም ቢሆን ወዳጁን ይወዳል፤ ወንድም የሚወለደው የወንድሙን ችግር ለመካፈል ነው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 17:22
ደስተኛነት ለልብ መልካም መድኃኒት ነው፤ የመንፈስ ሐዘንተኛ መሆን ግን አጥንትን ይሰብራል።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 17:9
የበደለን ሰው ይቅር የሚል ወዳጅነትን ያጸናል፤ በደልን መላልሶ የሚናገር ሰው ግን የቅርብ ወዳጆቹን ያጣል።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 17:27
ንግግሩን የሚቈጥብ ዐዋቂ ነው፤ የረጋ መንፈስ ያለውም ሰው አስተዋይ ነው።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 17:28
ሞኝ ዝም ሲል ጥበበኛ ይመስላል፤ ምንም ሳይናገር ቢቀር እንደ ብልኅ ይቈጠራል።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 17:1
ጥልና ክርክር በበዛበት ቤት በታላቅ ግብዣ ላይ ከመገኘት ይልቅ ሰላም ባለበት ቤት ደረቅ የዳቦ ቊራሽ መመገብ ይሻላል።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 17:14
የጥል መነሻ መፍረስ እንደ ጀመረ ግድብ ነው፤ ስለዚህ ጥል ከማስከተሉ በፊት ክርክርን አቁም።
8
መጽሐፈ ምሳሌ 17:15
በንጹሕ ሰው ላይ መፍረድ፥ ወይም በደለኛውን ንጹሕ ማድረግ ሁለቱም እግዚአብሔር የሚጸየፋቸው ድርጊቶች ናቸው።
Home
Bible
Plans
Videos