1
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:13-14
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ወንድሞቼ ሆይ! ገና ወደዚያ እንደ ደረስኩ አልቈጥርም፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ ይኸውም በስተኋላዬ የነበረውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እተጋለሁ። ሽልማቴንም ለማግኘት በፊቴ ወዳለው ግብ እሮጣለሁ፤ ይህም ሽልማት እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ወደ ላይ ጠርቶ የሚሰጠኝ ሕይወት ነው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:10-11
ሌላው ምክንያት ክርስቶስንና የክርስቶስን የትንሣኤ ኀይል ለማወቅ፥ የመከራው ተካፋይ ለመሆንና በሞቱም እርሱን ለመምሰል ነው። እንዲሁም ከሞትኩ በኋላ ተነሥቼ ለዘለዓለም በሕይወት ለመኖር ተስፋ በማድረግ ነው።
3
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:8
ከዚህም በቀር ጌታዬን ኢየሱስ ክርስቶስን ከማወቅ የበለጠ ሌላ ምንም ነገር እንደሌለ ስለማምን ሁሉን ነገር እንደ ኪሣራ እቈጥረዋለሁ፤ ስለ እርሱም ሁሉን ነገር አጥቻለሁ። ክርስቶስንም ለማግኘት ስል ሁሉን ነገር እንደ ቤት ጥራጊ እቈጥራለሁ።
4
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:7
እንግዲህ ከዚህ በፊት ጠቃሚዎች ናቸው ብዬ አምንባቸው የነበሩትን ነገሮች ሁሉ ስለ ክርስቶስ ብዬ ዋጋ እንደሌላቸው ከንቱ ነገሮች አድርጌ እቈጥራቸዋለሁ።
Home
Bible
Plans
Videos