1
የሉቃስ ወንጌል 11:13
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ነገር መስጠትን ካወቃችሁ በሰማይ የሚኖር አባታችሁማ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም!”
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
የሉቃስ ወንጌል 11:9
“ስለዚህ እኔም እናንተን የምላችሁ ይህን ነው፤ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤
3
የሉቃስ ወንጌል 11:10
የሚለምን ሁሉ ይቀበላል፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ መዝጊያ ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል።
4
የሉቃስ ወንጌል 11:2
ኢየሱስም “ስትጸልዩ እንዲህ በሉ አላቸው፤ ‘[በሰማይ የምትኖር] አባታችን ሆይ! ስምህ ይቀደስ! መንግሥትህ ትምጣ!
5
የሉቃስ ወንጌል 11:4
እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፥ በደላችንን ይቅር በልልን፤ ወደ ፈተናም አታግባን’ [ከክፉ አድነን እንጂ።]”
6
የሉቃስ ወንጌል 11:3
የዕለት እንጀራችንን በየቀኑ ስጠን!
7
የሉቃስ ወንጌል 11:34
የሰውነትህ መብራት ዐይንህ ነው፤ ዐይንህ ጤናማ ከሆነ ሰውነትህ ሁሉ በብርሃን የተሞላ ይሆናል፤ ዐይንህ ግን ታማሚ ከሆነ መላ ሰውነትህ ሁሉ ጨለማ ይሆናል።
8
የሉቃስ ወንጌል 11:33
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “መብራት አብርቶ በስውር ቦታ የሚያስቀምጠው፥ ወይም እንቅብ የሚደፋበት ማንም የለም፤ ይልቅስ ሰዎች ወደ ውስጥ ሲገቡ እንዲታያቸው ከፍ አድርጎ በመቅረዝ ላይ ያኖረዋል።
Home
Bible
Plans
Videos