1
የያዕቆብ መልእክት 4:7
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ስለዚህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙት፤ እርሱም ከእናንተ ይሸሻል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
የያዕቆብ መልእክት 4:8
ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል፤ እናንተ ኃጢአተኞች! እጆቻችሁን አጽዱ፤ እናንተ ወላዋዮች! ልባችሁን አጥሩ።
3
የያዕቆብ መልእክት 4:10
በጌታ ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ያደርጋችኋል።
4
የያዕቆብ መልእክት 4:6
ሆኖም መጽሐፍ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ስለሚል እግዚአብሔር የሚሰጠው ጸጋ ከሁሉም ይበልጣል።
5
የያዕቆብ መልእክት 4:17
እንግዲህ መልካም ነገር ማድረግን እያወቀ የማያደርግ ሰው አለማድረጉ ኃጢአት ይሆንበታል።
6
የያዕቆብ መልእክት 4:3
ብትጸልዩም የጸሎታችሁን መልስ የማታገኙት የለመናችሁትን ነገር በሥጋዊ ደስታ ላይ ለማዋል በክፉ ሐሳብ ስለምትጸልዩ ነው።
7
የያዕቆብ መልእክት 4:4
እናንተ ከዳተኞች! ዓለምን የሚወድ የእግዚአብሔር ጠላት መሆኑን አታውቁምን? እንግዲህ ዓለምን የሚወድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት መሆኑ ነው።
8
የያዕቆብ መልእክት 4:14
ነገ የሚሆነውን አታውቁም፤ ሕይወታችሁ ምንድን ነው? ለአንድ አፍታ ታይቶ በኋላ እንደሚጠፋ ጉም ናችሁ።
Home
Bible
Plans
Videos