1
ትንቢተ ኢሳይያስ 45:3
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
በጨለማና በድብቅ ቦታ የተከማቸውን ሀብት እሰጥሃለሁ። በዚህም በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንኩ ታውቃለህ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 45:2
“እኔ በፊትህ እሄዳለሁ፤ ተራራዎችን ዝቅ አድርጌ እደለድላለሁ፤ በነሐስ የተሠሩ በሮችንና የብረት መወርወሪያዎችን እሰብራለሁ።
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 45:5-6
“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ አንተ እኔን ባታውቀኝም እንኳ ብርታትን እሰጥሃለሁ። ይህንንም የማደርገው መላው ዓለም እኔ ብቻ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩና ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ያውቅ ዘንድ ነው።
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 45:7
እኔ ጨለማንና ብርሃንን እፈጥራለሁ፤ ደኅንነትንና ወዮታን አመጣለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አደርጋለሁ።
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 45:22
“ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ ስለሌለ፥ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ያላችሁ ሁሉ ወደ እኔ ተመልሳችሁ ደኅንነትን አግኙ።
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 45:1
ሕዝቦች በሥልጣኑ ሥር እንዲገዙ ለማድረግ፥ ነገሥታትን ከሥልጣን እንዲያወርድ፥ የከተሞችን ቅጽር በሮች ይከፍትለት ዘንድ ቀኝ እጁን ለያዘውና ቀብቶ ላነገሠው ንጉሥ ቂሮስን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፦
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 45:23
የማይለወጥ እውነተኛ የተስፋ ቃል ስሰጥ በራሴ ምዬ ነው። ስለዚህ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ አንደበትም ሁሉ በእኔ ስም ይምላል።
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 45:4
የመረጥኳቸውን የያዕቆብን ልጆች እስራኤላውያንን እንድትረዳ፥ አንተ እኔን ባታውቀኝም እንኳ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ የማዕርግ ስምም ሰጥቼሃለሁ።
Home
Bible
Plans
Videos