1
ትንቢተ ዳንኤል 2:20-22
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
“ጥበብም ኀይልም የእርሱ ስለ ሆነ እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን! እርሱ ጊዜያትንና ወራትን ያፈራርቃል፤ ነገሥታትን ወደ ዙፋን ያወጣል፤ ከዙፋንም ያወርዳል፤ ጥበብን ለጠቢባን፥ ዕውቀትንም ለአስተዋዮች የሚሰጥ እርሱ ነው። እርሱ ጥልቅ የሆነውን ምሥጢርና የተሰወረውን ነገር ይገልጣል፤ በእርሱ ዘንድ ሁልጊዜ ብርሃን ስላለ፥ በጨለማ የተሰወረውን ያውቃል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ዳንኤል 2:27-28
ዳንኤልም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ንጉሥ ሆይ! አንተ የጠየቅኸውን ምሥጢር ጠቢባንም ሆኑ አስማተኞች፤ ጠንቋዮችም ሆኑ መተተኞች ሊነግሩህ አይችሉም። ነገር ግን ምሥጢርን ሁሉ የሚገልጥ አንድ አምላክ በሰማይ አለ፤ እርሱ ወደ ፊት የሚሆነውን ነገር ሁሉ ለአንተ ገልጦልሃል፤ በአልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለ ያየኸው ሕልምና በአእምሮህ የነበረው ራእይ የሚከተለው ነው።
3
ትንቢተ ዳንኤል 2:44
በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይፈርስና ግዛቱም በሌላ ሕዝብ የማይደፈር መንግሥትን ይመሠርታል፤ ይህ መንግሥት ሌሎችን መንግሥታት እስከ መጨረሻው ያጠፋቸዋል፤ እርሱ ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤
Home
Bible
Plans
Videos