1
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:13
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ይቅር በሉ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:2
ዘወትር በላይ በሰማይ ስላሉት ነገሮች አስቡ እንጂ በምድር ላይ ስላሉት ነገሮች አታስቡ።
3
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:23
የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ ኢየሱስ እንደምታደርጉት ዐይነት ከልባችሁ አድርጉት።
4
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:12
እንግዲህ የእግዚአብሔር ምርጦችና ቅዱሳን፥ የተወደዳችሁም እንደ መሆናችሁ መጠን ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትሕትናን፥ ገርነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ።
5
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:16-17
የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ። በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት፤ በእርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑ።
6
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:14
ከዚህም ሁሉ በላይ ሁሉን ነገር ሰብስቦ በማሰር ፍጹም አንድነትን የሚያስገኘውን ፍቅርን ልበሱ።
7
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:1
እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከሞት ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ በሰማይ ያሉትን ነገሮች ፈልጉ።
8
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:15
የአንድ አካል ክፍሎች ሆናችሁ በእርግጥ የተጠራችሁት ለዚህ ሰላም ስለ ሆነ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገሥ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።
9
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:5
ስለዚህ በእናንተ የሚገኙትን የምድራዊ ሕይወት ምኞቶች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም “ዝሙት፥ ርኲሰት፥ ፍትወት፥ ክፉ ምኞት፥ ጣዖት ማምለክ የሆነ መጐምጀት” ናቸው።
10
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:3
እናንተ በሞት የመለየትን ያኽል ከዚህ ዓለም ተለይታችኋል፤ ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ውስጥ ተሰውሮአል።
11
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:8
አሁን ግን ቊጣን፥ ንዴትን፥ ተንኰልን፥ ስም ማጥፋትን ከእናንተ አስወግዱ፤ የሚያሳፍር ንግግርም ከአፋችሁ አይውጣ።
12
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:9-10
አሮጌውን ባሕርይ ከነሥራው አውልቃችሁ ስለ ጣላችሁት እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ። በፈጣሪው አምሳል በዕውቀት እየታደሰ የሚሄደውን አዲሱን ባሕርይ ልበሱ።
13
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:19
ባሎች ሆይ! ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ ጨካኞችም አትሁኑባቸው።
14
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:20
ልጆች ሆይ! ይህ ጌታን ደስ የሚያሰኝ ስለ ሆነ በሁሉ ነገር ለወላጆቻችሁ ታዘዙ።
15
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:18
ሚስቶች ሆይ! በጌታ ዘንድ ተገቢ ስለ ሆነ ለባሎቻችሁ ታዘዙ።
Home
Bible
Plans
Videos