1
2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:3
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ማንም ሰው በምንም ዐይነት አያታላችሁ፤ አስቀድሞ ክሕደት ሳይመጣ፥ ገሃነም የሚገባው የዐመፅ ሰው የሆነውም ሳይገለጥ፥ ያ ቀን አይመጣም።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:13
በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ማመስገን ይገባናል፤ የምናመሰግነውም እናንተ በመንፈስ ቅዱስ በመቀደሳችሁና እውነትን በማመናችሁ እንድትድኑ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ስለ መረጣችሁ ነው።
3
2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:4
ይህ የዐመፅ ሰው አማልክት ተብለው ከሚመለኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ያደርጋል፤ “እግዚአብሔር ነኝ” እያለም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንኳ ለመቀመጥ ይደፍራል።
4
2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:16-17
ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን፥ በጸጋውም የዘለዓለም መጽናናትን፥ መልካም ተስፋንም የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን መልካም የሆነውን ሁሉ እንድታደርጉና እንድትናገሩ ልባችሁን ያጽናናው፤ መልካሙን ነገር ሁሉ እንድታደርጉና እንድትናገሩ ያበርታችሁ።
5
2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:11
በዚህ ምክንያት በሐሰት እንዲያምኑ እግዚአብሔር የሚያሳስት ኀይልን ይልክባቸዋል።
6
2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:9-10
የዐመፅ ሰው የሚመጣው በሰይጣን ኀይል አሳሳች ተአምራትንና ምልክቶችን አስደናቂ ነገሮችንም በማድረግ ነው፤ እንዲሁም የሚጠፉትን ሰዎች የሚያታልሉት ማናቸውንም ክፉ ነገሮችን በማድረግ ነው። እነዚህ ሰዎች የሚጠፉትም ለመዳን የሚያበቃቸውን እውነት ወደው ስላልተቀበሉ ነው።
7
2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:7
ምሥጢራዊው የዐመፅ ኀይል አሁንም በመሥራት ላይ ነው፤ ሆኖም አሁን የሚከለከለው አለ፤ ይህም የሚሆነው ያ የሚከለክለው እስኪወገድ ድረስ ነው።
Home
Bible
Plans
Videos