1
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5:16-18
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ባለማቋረጥ ጸልዩ፤ በሁሉ ነገር እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ሕይወት እግዚአብሔር ከእናንተ የሚፈልገው ይህን ነው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5:23-24
ራሱ የሰላም አምላክ በሁሉ ነገር ይቀድሳችሁ፤ መንፈሳችሁ፥ ነፍሳችሁ፥ አካላችሁ በሙሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚመጣበት ቀን ያለ ነቀፋ ተጠብቆ ይኑር። ያ የሚጠራችሁ ታማኝ ስለ ሆነ ይህን ያደርገዋል።
3
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5:15
ማንም ሰው በክፉ ፋንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ይልቅስ ሁልጊዜ እናንተ ለእርስ በርሳችሁም ሆነ እንዲሁም ለሌሎች ሰዎች ሁሉ መልካም ለማድረግ ትጉ።
4
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5:11
ስለዚህ አሁን በምታደርጉት ዐይነት አንዱ ሌላውን በማነጽ ያበረታታው።
5
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5:14
ወንድሞች ሆይ! “ሰነፎችን ገሥጹ፤ ፈሪዎችን አደፋፍሩ፤ ደካሞችን እርዱ፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ” ብለን እንመክራችኋለን።
6
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5:9
እግዚአብሔር የጠራን ለቊጣ ሳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት መዳንን እንድናገኝ ነው።
7
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5:5
እናንተ ሁላችሁም የብርሃን ሰዎች፥ የቀንም ሰዎች ናችሁ፤ እኛ የሌሊት ወይም የጨለማ ሰዎች አይደለንም።
Home
Bible
Plans
Videos