1
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 8:7
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፦ “ሕዝቡ የሚሉህን ነገር ሁሉ ተቀበል፤ እነርሱ የናቁት አንተን አይደለም፤ በእነርሱ ላይ ነግሼ እንዳልኖር፥ እነርሱ የናቁት እኔን ነው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 8:8
እኔ እነርሱን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ፊታቸውን መልሰው ከእኔ በመራቅ ባዕዳን አማልክትን ሲያመልኩ ኖረዋል፤ እንግዲህ በእኔ ላይ ሲያደርጉት የነበረውን ሁሉ እነሆ በአንተም ላይ መፈጸም ጀምረዋል፤
3
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 8:5-6
“እነሆ! አንተ በእርጅና ላይ ነህ፤ ልጆችህም የአንተን መልካም አርአያነት አልተከተሉም፤ ስለዚህ በሌሎች አገሮች እንደሚደረገው እኛን የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን።” ንጉሥ ያነግሥላቸው ዘንድ በመጠየቃቸውም ሳሙኤል አዝኖ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤
4
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 8:19
ይሁን እንጂ ሕዝቡ ሳሙኤል ለነገራቸው ቃል ሁሉ ዋጋ አልሰጡትም፤ ይልቁንም “እንደዚህ አይደለም! እኛ ንጉሥ እንዲኖረን እንፈልጋለን፤
Home
Bible
Plans
Videos