1
1 የዮሐንስ መልእክት 3:18
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ልጆች ሆይ! ፍቅራችን እውነተኛና በሥራ የሚገለጥ ይሁን እንጂ በቃል ወይም በንግግር ብቻ አይሁን።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
1 የዮሐንስ መልእክት 3:16
ፍቅር ምን እንደ ሆነ የምናውቀው ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወቱን ለእኛ አሳልፎ ስለ ሰጠን ነው፤ እኛም ሕይወታችንን ስለ ወንድሞቻችን አሳልፈን መስጠት ይገባናል።
3
1 የዮሐንስ መልእክት 3:1
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ! በእርግጥም የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ዓለም እግዚአብሔርን ስላላወቀ እኛንም አያውቀንም።
4
1 የዮሐንስ መልእክት 3:8
ዲያብሎስ ከመጀመሪያው አንሥቶ ኃጢአት ስለሚሠራ ኃጢአትን የሚሠራ ሁሉ የዲያብሎስ ወገን ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ነው።
5
1 የዮሐንስ መልእክት 3:9
የእግዚአብሔር ባሕርይ በውስጡ ስለሚኖርና ከእግዚአብሔርም ስለ ተወለደ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ኃጢአት አይሠራም፤ ሊሠራም አይችልም።
6
1 የዮሐንስ መልእክት 3:17
ሰው በዚህ ዓለም ሀብት እያለው ችግረኛውን አይቶ ባይራራለት “እግዚአብሔርን እወዳለሁ” ማለት እንዴት ይችላል?
7
1 የዮሐንስ መልእክት 3:24
የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚፈጽሙ ሁሉ በእግዚአብሔር ይኖራሉ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ይኖራል። እግዚአብሔር በእኛ መኖሩን የምናውቀው እርሱ በሰጠን መንፈስ ነው።
8
1 የዮሐንስ መልእክት 3:10
የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ተለይተው የሚታወቁት በዚህ ነው፦ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም።
9
1 የዮሐንስ መልእክት 3:11
ከመጀመሪያው የሰማችሁት መልእክት “እርስ በርሳችን እንፋቀር” የሚል ነው።
10
1 የዮሐንስ መልእክት 3:13
ወንድሞች ሆይ! ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ።
Home
Bible
Plans
Videos