1
መዝሙር 40:1-2
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት፤ እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማ። ከሚውጥ ጕድጓድ፣ ከሚያዘቅጥ ማጥ አወጣኝ፤ እግሮቼን በዐለት ላይ አቆመ፤ አካሄዴንም አጸና።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መዝሙር 40:3
ለአምላካችን የሚሆን ውዳሴ፣ አዲስ ዝማሬን በአፌ ላይ አኖረ፤ ብዙዎች ያያሉ፤ ይፈራሉም፤ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
3
መዝሙር 40:4
እግዚአብሔርን መታመኛው ያደረገ፣ ወደ ትዕቢተኞች የማይመለከት፣ የሐሰት አማልክትን ወደሚከተሉት የማያይ ሰው ብፁዕ ነው።
4
መዝሙር 40:8
አምላኬ ሆይ፤ ፈቃድህን ላደርግ እሻለሁ፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ አለ።”
5
መዝሙር 40:11
እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አትንፈገኝ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ፤
Home
Bible
Plans
Videos