1
ምሳሌ 1:7-8
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፤ ተላሎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ምክር አድምጥ፤ የእናትህንም ትምህርት አትተው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ምሳሌ 1:32-33
ብስለት የሌላቸውን ስድነታቸው ይገድላቸዋል፤ ተላሎችንም ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል፤ የሚያዳምጠኝ ሁሉ ግን በሰላም ይኖራል፤ ክፉን ሳይፈራ ያለ ሥጋት ይቀመጣል።”
3
ምሳሌ 1:5
ጥበበኞች ያድምጡ፤ ትምህርታቸውንም ያዳብሩ፤ አስተዋዮችም መመሪያ ያግኙበት፤
4
ምሳሌ 1:10
ልጄ ሆይ፤ ኀጢአተኞች ቢያባብሉህ፣ እሺ አትበላቸው፤
5
ምሳሌ 1:1-4
የእስራኤል ንጉሥ፣ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች፤ ጥበብንና ተግሣጽን ለመቀበል፤ ጥልቅ ሐሳብ የሚገልጡ ቃላትን ለማስተዋል፤ ጽድቅን፣ ፍትሕንና ሚዛናዊ ብያኔን በማድረግ፣ የተገራ ጠቢብ ልቦናን ለማግኘት፤ ብስለት ለሌላቸው አስተዋይነትን፣ በዕድሜ ለጋ ለሆኑት ዕውቀትንና ልባምነትን ለመስጠት፤
6
ምሳሌ 1:28-29
“በዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፤ እኔ ግን አልመልስላቸውም፤ አጥብቀው ይፈልጉኛል፤ ነገር ግን አያገኙኝም። ዕውቀትን ስለ ጠሉ፣ እግዚአብሔርንም መፍራት ስላልመረጡ፣
Home
Bible
Plans
Videos