1
መክብብ 4:9-10
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ለሥራቸው መልካም ውጤት ስለሚያገኙ፣ ከአንድ፣ ሁለት መሆን ይሻላል፤ አንዱ ቢወድቅ፣ ባልንጀራው ደግፎ ያነሣዋል። ቢወድቅ የሚያነሣው ረዳት የሌለው ግን፣ እንዴት አሳዛኝ ነው!
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መክብብ 4:12
አንድ ሰው ብቸኛውን ቢያጠቃውም፣ ሁለት ከሆኑ ይመክቱታል፤ በሦስት የተገመደ ገመድም ቶሎ አይበጠስም።
3
መክብብ 4:11
ደግሞም ሁለቱ አብረው ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ ነገር ግን አንዱ ብቻውን እንዴት ሊሞቀው ይችላል?
4
መክብብ 4:6
በድካምና ነፋስን በመከተል ከሚገኝ ሁለት ዕፍኝ ይልቅ፣ በርጋታ የሚገኝ አንድ ዕፍኝ ይሻላል።
5
መክብብ 4:4
እንዲሁም ጥረትና የሥራ መከናወን ሁሉ ሰው በባልንጀራው ላይ ካለው ቅናት እንደሚመነጭ ተመለከትሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
6
መክብብ 4:13
ምክርን መቀበል ከማያውቅ ሞኝና ሽማግሌ ንጉሥ ይልቅ ጠቢብ የሆነ ድኻ ወጣት ይሻላል።
Home
Bible
Plans
Videos