1
ዘዳግም 11:19
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው፤ ቤት ስትቀመጥ፣ መንገድ ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣ ስለ እነዚሁ አጫውታቸው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ዘዳግም 11:18
እነዚህን ቃሎቼን፣ በልባችሁና በአእምሯችሁ አኑሯቸው፤ በእጆቻችሁ ላይ ምልክት አድርጋችሁ እሰሯቸው፣ በግምባራችሁም ላይ ይሁኑ።
3
ዘዳግም 11:13-14
ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች በታማኝነት ብትጠብቁ፣ ይኸውም አምላካችሁን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ብትወዱና በፍጹም ልባችሁ፣ በፍጹም ነፍሳችሁም እርሱን በማገልገል በታማኝነት ብትጠብቁ፣ እህልህን፣ ወይንህንና ዘይትህን እንድትሰበስብ የበልጉንና የክረምቱን ዝናብ በምድርህ ላይ በየወቅቱ አዘንባለሁ።
4
ዘዳግም 11:1
እንግዲህ አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ውደድ፤ ግዴታውን፣ ሥርዐቱን፣ ሕጉንና ትእዛዙን ሁልጊዜ ጠብቅ።
5
ዘዳግም 11:26-28
እነሆ፤ ዛሬ በረከትንና መርገምን በፊታችሁ አኖራለሁ፤ በረከቱ ዛሬ የምሰጣችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ትእዛዞች ስትፈጽሙ ሲሆን፣ መርገሙ ደግሞ፣ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ትእዛዞች የማትፈጽሙ፣ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ለመከተል እኔ ከማዝዛችሁ መንገድ የምትወጡ ከሆነ ነው።
6
ዘዳግም 11:20-21
በቤትህ መቃኖችና በግቢህ በሮች ላይ ጻፋቸው፤ ይህን ካደረጋችሁ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ለአባቶቻችሁ ለመስጠት በማለላቸው ምድር የእናንተና የልጆቻችሁ ዘመን ከምድር በላይ ያሉ ሰማያትን ርቀት ያህል ይሆናል።
7
ዘዳግም 11:16
ተጠንቀቁ፤ አለዚያ ተታልላችሁ ሌሎች አማልክትን ታመልካላችሁ፤ ትሰግዳላችሁም።
Home
Bible
Plans
Videos