1
2 ነገሥት 20:5
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
“ተመለስና የሕዝቤን አለቃ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፤ ‘የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፤ እፈውስሃለሁ። ከዛሬ ሦስት ቀን በኋላ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
2 ነገሥት 20:3
“እግዚአብሔር ሆይ፤ በታማኝነትና በፍጹም ልብ በፊትህ እንደ ሄድሁ፣ አንተን ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ዐስብ፤” ሕዝቅያስም ምርር ብሎ አለቀሰ።
3
2 ነገሥት 20:1
በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ሊሞት ተቃርቦ ነበር። የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ እርሱ ሄዶ፣ “እግዚአብሔር፣ ‘ትሞታለህ፤ ከእንግዲህ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል’ ብሎሃል” አለው።
4
2 ነገሥት 20:6
በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምርልሃለሁ፤ አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ስለ እኔ ስለ ራሴና ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ስል ይህችን ከተማ እከላከልላታለሁ።’ ”
Home
Bible
Plans
Videos