1
2 ዜና መዋዕል 20:15
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እርሱም እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ ኢዮሣፍጥ፣ እናንተም በይሁዳና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ! እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል፤ ‘ውጊያው የእግዚአብሔር እንጂ የእናንተ አይደለምና፣ ከዚህ ታላቅ ሰራዊት የተነሣ አትፍሩ፣ አትደንግጡ፣
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
2 ዜና መዋዕል 20:17
ይህን ጦርነት የምትዋጉት እናንተ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር የሚሰጣችሁንም ማዳን እዩ። አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ነገውኑ ውጡና ግጠሟቸው፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሆናል።’ ”
3
2 ዜና መዋዕል 20:12
አምላካችን ሆይ፤ አንተ አትፈርድባቸውምን? የመጣብንን ይህን ታላቅ ሰራዊት እንቋቋም ዘንድ ዐቅም የለንምና የምናደርገውን አናውቅም፤ ነገር ግን ዐይኖቻችን ወዳንተ ናቸው።”
4
2 ዜና መዋዕል 20:21
ከሕዝቡም ጋር ከተመካከረ በኋላ ከሰራዊቱ ፊት ቀድመው በመሄድ፣ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፣ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና” እያሉ ለእግዚአብሔር የሚዘምሩና ስለ ቅድስናውም ክብር የሚያወድሱ ሰዎችን መደበ።
5
2 ዜና መዋዕል 20:22
መዘመርና ማወደስ እንደ ጀመሩም፣ እግዚአብሔር ይሁዳን በወረሩት በአሞን፣ በሞዓብና በሴይር ተራራ ሰዎች ላይ ድብቅ ጦር አመጣባቸው፤ ተሸነፉም።
6
2 ዜና መዋዕል 20:3
ኢዮሣፍጥም እጅግ ስለ ፈራ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም ዐወጀ።
7
2 ዜና መዋዕል 20:9
‘የፍርድ ሰይፍም ሆነ የቸነፈር ወይም የራብ መከራ ቢደርስብን፣ ስምህ በተጠራበት በዚህ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት፣ በፊትህ ቆመን በጭንቀታችን ወደ አንተ እንጮሃለን፤ አንተም ትሰማናለህ፤ ታድነናለህም።’
8
2 ዜና መዋዕል 20:16
ነገ በእነርሱ ላይ ውረዱ፤ እነርሱ በጺጽ መተላለፊያ ሽቅብ ይወጣሉ፣ እናንተም በይሩኤል ምድረ በዳ ውስጥ በሸለቆው መጨረሻ ላይ ታገኟቸዋላችሁ።
9
2 ዜና መዋዕል 20:4
የይሁዳ ሕዝብም የእግዚአብሔርን ርዳታ ይሻ ዘንድ በአንድነት ተሰበሰበ፤ ከይሁዳ ከተሞች ሁሉም እግዚአብሔርን ለመፈለግ መጡ።
Home
Bible
Plans
Videos