1
1 ዜና መዋዕል 16:11
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ወደ እግዚአብሔርና ወደ ኀይሉ ተመልከቱ፤ ዘወትር ፊቱን ፈልጉ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
1 ዜና መዋዕል 16:34
ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
3
1 ዜና መዋዕል 16:8
ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ለአሕዛብ ያደረገውን ሁሉ ንገሩ፤
4
1 ዜና መዋዕል 16:10
በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ልባቸው ሐሤት ያድርግ።
5
1 ዜና መዋዕል 16:12
ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣ ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤
6
1 ዜና መዋዕል 16:9
ዘምሩለት፤ ውዳሴም አቅርቡለት፤ ድንቅ ሥራውን ሁሉ ንገሩ፤
7
1 ዜና መዋዕል 16:25
እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ ምስጋናውም ብዙ ነው፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ የሚገባው ነው።
8
1 ዜና መዋዕል 16:29
ለስሙ የሚገባውን ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤ መባ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ፤ በቅድስናውም ክብር ለእግዚአብሔር ስገዱ።
9
1 ዜና መዋዕል 16:27
በፊቱ ክብርና ሞገስ አለ፤ ብርታትና ደስታም በማደሪያው ስፍራ።
10
1 ዜና መዋዕል 16:23
ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ማዳኑንም ዕለት ዕለት ዐውጁ።
11
1 ዜና መዋዕል 16:24
ክብሩን ለአሕዛብ ተናገሩ፤ ድንቅ ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ።
12
1 ዜና መዋዕል 16:22
እንዲህ ሲል፤ “የቀባኋቸውን አትንኩ፤ በነቢያቴ ላይ ክፉ አታድርጉ።”
13
1 ዜና መዋዕል 16:26
የአሕዛብ ሁሉ አማልክት ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
14
1 ዜና መዋዕል 16:15
ኪዳኑን እስከ ዘላለም፣ ያዘዘውንም ቃል እስከ ሺሕ ትውልድ ያስባል።
15
1 ዜና መዋዕል 16:31
ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድር ሐሤት ታድርግ፤ በአሕዛብም መካከል፤ “እግዚአብሔር ነገሠ!” ይበሉ።
16
1 ዜና መዋዕል 16:36
ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ፣ “አሜን፤ እግዚአብሔር ይመስገን” አሉ።
17
1 ዜና መዋዕል 16:28
የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ክብርና ኀይልን ለእግዚአብሔር አምጡ።
Home
Bible
Plans
Videos